Building and Finishing Materials

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የኮንክሬት ሚክስ ምርት በቁርጥ ዋጋ መግዛት ይፈልጋል

Description

የኮንክሪት ሚክስ የቁርጥ ዋጋ ግዥ
ጥሪ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚያከናውነው አስቸኳይ ፕሮጅክቶች ግብዓት የሚያገለግል የኮንከሬት ሚክስ ምርት በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የምርቱ አይነት

መለኪያ

ብዛት

የአንድ ሜ.ኪ ነጠላ ዋጋ + ትራንስፖርት+ ተ.እ.ታ ጨምሮ

1

Concrete C-25 Without Pump

ሜ.ኩ

25,141

18,105.03

2

Concrete C-30 Without Pump

ሜ.ኩ

6,949

18,735.03

3

Concrete C-30 With Pump

ሜ.ኩ

2,434

19,285.03

1. አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።

2. የኮንክሪት ሚክስ ማምረቻ ማሽን የባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ሕጋዊ ውክልና፤ በሕግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ የኮንክሪት ሚክስ ለማምረትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ፣ ወይም ኮንክሪት ሚክስ ለማምረትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ ካለው ግለሰብ/ማህበር የተሰጠ ሕጋዊ/በፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት የተረጋገጠ/ ውክልና አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቹ ለእያንዳንዱ የኮንክሪት ምርት አይነት በቀን ቢያንስ 40 ሜ.ኬ ወይም ከሶስትም የምርት አይነቶች በድምሩ ቢያንስ በቀን 120 ሜ.ኩ እና ከዚያ በላይ ምርት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

4. የሚቀርበው ምርት በባለሥልጣን መ/ቤቱ የጥራት መመዘኛ መስፈርት /specification/ መሰረት መሆኑ መ/ቤቱ የላብራቶሪ የጥራት ፍተሻ ያከናወናል።

5. አቅራቢው የኮንክሪት አይነቶች ሚክስ ዲዛይን ዶክመንት፤ የኮንክሪት ጠጠር እና አሸዋ የጥራት ማረጋገጫ ላብራቶሪ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባለፉት ስድስት ወራት ግዜ ውስጥ ፍቃድ ካለው የላብራቶሪ ማዕከል ወይም ተጫራቹ በራሱ ላብራቶሪ የተከናወነ ሆኖ ሕጋዊ ሥልጣን ባለው ተቋም/አማካሪ የተረጋገጠ ዶክመንት ሪፖርት ማቅረብ አለበት።

6. አቅራቢው ውል በተዋዋለ በ3 ቀን ውስጥ አቅርቦት መጀመር አለበት።

7. ተጫራቾች ኮንክሪት ማምረቻ ማሽኑን በሚመለከት የማሽኑን የማምረት አቅም የሚገልፅ ቴክኒካል ሰነድ /ሊብሬ/ማቅረብ አለበት የኮንክሪት ባቺንግ ፕላንቱ ዝቅተኛ የማምረት አቅሙ 30m3 /Hr መሆኑ አለበት ማረጋገጫ በፅሁፍ ማቅረብ አለባቸው።

8. በአገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ከ15% በላይ ሲጨምር ወይም ሲቀንስ ኮንክሪት ሚክስ ማጓጓዣ የትራንስፖርት ወጪ ላይ ብቻ ከ7ሜ.ኩ እስከ  10ሜ.ኩ በሚጭኑ የትራክ ሚክሰሮችን ለ1 ኪ.ሜትር ደርሶ መልስ 1.18ሊትር የነዳጅ ፍጆታ ተመን መሰረት ማስተካከያ የሚደረግ ይሆናል።

9. አቅራቢዎች ለምዝገባ በሚቀርቡበት ቅደም ተከተል መሰረት የመ/ቤቱ ፍላጎት እስኪሟላ ድረስ ይስተናገዳሉ።

10. አቅራቢዎች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀን እና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 023 ከላይ የተገለፁትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።

ባለሥልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የግዥ ፍላጎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-3-72-28-25/011-3-71-41-03
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-23
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Bid opening: 2026-11-23 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Roads Authority
  • Buyer's registered address: አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ
  • Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
  • Posted at: 2026-11-06T08:10:45.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders