Building and Finishing Materials

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የኮንክሬት ቱቦ (RC Pipe 48 ዲያሜትር) መግዛት ይፈልጋል

Description

የኮንክሪት ቱቦ (RC Pipe 48 ዲያሜትር) ምርት የቁርጥ ዋጋ ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚያከናውነው አስቸኳይ ፕሮጀክቶች ግብዓት የሚያገለግል የኮንክሬት ቱቦ (RC-PiPe 48 Ø) ምርት በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የምርቱ ዓይነት

መለኪያ

 

ብዛት

 

የአንድ ሜትር ነጠላዋጋ+ ትራንስፖርት+ተ.እ.ታ ጨምሮ

1

የኮንክሬት ቱቦ (RC-PiPe 48 Ø ምርት

ሜትር

5,700

37,704.25 ብር

1. አግባነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።

2. የኮንክሪት ቱቦ ማምረቻ ማሽኑ ባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ሕጋዊ ውክልና እንዲሁም በሕግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ ኮንክሪት ቱቦ ለማምረትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ፣ ወይም ኮንክሪት ቱቦ ለማምረትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ ካለው ግለሰብ/ማህበር የተሰጠ ሕጋዊ/በፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ ቤት የተረጋገጠ/ ውክልና አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።

3. አቅራቢው ቢያንስ በቀን 100 ሜትር ባለ 2ሜትር እና ከዚያ በላይ ርዝመት ያለው የኮንክሪት ቱቦ አምርቶ ማቅረብ አለበት።

4. የሚቀርበው ምርት በባለሥልጣን መ/ቤቱ የጥራት መመዘኛ መስፈርት /specification/ መሰረት መሆኑ መ/ ቤቱ በላብራቶሪ የጥራት ፍተሻ ያከናውናል።

5. አቅራቢዎች የኮንክሬት ቱቦ (RC-PiPe 48 Ø) ምርት በሚሰጣቸው ድልድል መሰረት አጓጉዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. በአገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ከ15% በላይ ሲጨምር ወይም ሲቀንስ የመጫን አቅሙ ማጓጓዣ የትራንስፖርት ወጪ ላይ ብቻ 33.8ሜትር (48in) በሚጭኑ ተሽከርካሪዎች ለ 1ኪሎ ሜትር ደርሶ መልስ 2ሊትር የነዳጅ ፍጆታ ተመን መሰረት ማስተካከያ የሚደረግ ይሆናል።

7. አቅራቢዎች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀን እና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 023 ከላይ የተገለፁትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።

ባለሥልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የግዥ ፍላጎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-3-72-28-25/011-3-71-41-03
ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ አጠገብ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-23
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Bid opening: 2026-11-23 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Roads Authority
  • Buyer's registered address: አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ
  • Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
  • Posted at: 2026-11-06T08:20:23.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders