Equipment and Accessories

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ ኮንስትራከሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

 የግልፅ እና የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ

  • የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣
  • የቤት ማስዋቢያ፣
  • የቤት ዕቃ
  • ኮንስትራከሽን፣ 
  • አልባሳት፣
  • እስፔርፓርት፣
  • የፅዳት ዕቃ፣
  • ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች 01/03/2019 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች :-

  1. በዘርፋ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. ለሀራጅ ጨረታው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  4. በሀራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
  5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
  6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃ ክፍያውን በO5 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤
  7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) በመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  8. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ወዲያውኑ ይመሰስላቸዋል፤
  9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
  10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
  11. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
  12. ተጫራች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከቀን 01/03/2019 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቀረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ03/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:45 ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
  13. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው 03/03/2019 ከጠዋቱ 4፡15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤
  14. N.B:- አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።

 የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-12
  • Bid closing time: 10:15
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-12 10:15
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Somali
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
  • Posted at: 2026-11-06T08:35:35.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders