Office Furniture

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የፋይናንስ ሰነድ ማስቀመጫ ሼልፍ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ኢፕድ 0012/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የፋይናንስ ሰነድ ማስቀመጫ ሼልፍ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በዉድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸዉ።

2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ግዥዉን አስመልክቶ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምርያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመዉሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀዉ በአቅርቦት መምርያ ግዥ ቡድን በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።

3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ የሚውል ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድቦንድ | ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸዉ አካል የሚሰጥ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ አለባቸዉ\።

4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምርያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምርያ ይከፈታል :ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለዉ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ስልክ ቁጥር 011 156 9869
ኢሜይል [email protected] 
አድራሻ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም መተሚያ ድርጅት ፊትለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምርያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-11-23 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምርያ ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Press Agency
  • Buyer's registered address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
  • Posted at: 2026-11-07T07:46:04.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders