Equipment and Accessories

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ለስልጠና የሚያስፈልጉ ግብዓቶች፣ የንፅህና መስጫ ሳሙና፣ ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል የውስጥ ሱሪ እና ሞዴስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥው መለያ ቁጥር BO/ ግፋን/11/2019

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ የፕሮጀክቱ ስም በዩኒሴፍ በጀት የሚገዙ እና አገልግሎት የሚዉል

  • ሎት አንድ ለስልጠና የሚያስፈልጉ ግብዓቶች
  • ሎት ሁለት የንፅህና መስጫ ሳሙና
  • ሎት ሶስት ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል የውስጥ ሱሪ
  • ሎት አራት ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል እንደገና ታጥቦ ጥቅም ላይ የሚውል ሞዴስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

  1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ
  2. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸዉ
  4. የግዥው መጠን ብር ከ500,000/አምስት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ፡፡
  5.  የምዝገባ የምስክር ወረቀት
  6.   የሙያ ብቃት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ለሎት 3 እና ሊሎት 4
  7. የመልካም ስራ አፈፃፀም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ለሎት 3 እና ለሎት 4
  8. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-7 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰነድ መግዛት እና መውሰድ ይቻላል ፡፡
  10. የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ
    • ሎት አንድ ለስልጠና የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ብር 50,000.00፣
    • ሎት ሁለት የንፅህና መስጫ ሳሙና ብር 50,000.00፣
    • ሎት ሶስት ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል የውስጥ ሱሪ ብር 150,000.00 እና
    • ሎት አራት ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል እንደገና ታጥቦ ጥቅም ላይ የሚውል ሞዴስ ብር 150,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ::
  12. የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታዉ ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልፅ ጨረታ የሚል ተጽፎበት ጨረታዉ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት እና በ11ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን መግባት ይኖርበታል፡፡
  13. ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በትም ቢሮ አዳራሽ ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
  14. የጨረታ መክፈቻዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበአል ቀን ከሆነ ጨረታዉ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናለ፡፡
  15. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቁጥር 058 222 0814 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 62 67/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
  16. ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበ ነዉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-20
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታዉ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት እና በ11ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-20 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታዉ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት እና በ11ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Region Education Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T10:57:55.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders