Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት አግልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2019

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት አግልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1. የጽህፈት መሣሪያዎች፣
  • ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 4. ፈርኒቸር፣
  • ሎት 5. የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 6. የብስክሌት ጎማና ካለማደሪያ፣
  • ሎት 7. የመኪና ጎማና ካለማደሪያ፣
  • ሎት 8. የተሸከርካሪ መለዋወጫ እና ድኮር ግዥ ለመፈፀም ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡-

  1.  አቅራቢዎች ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ (የሥራ) ፈቃድ፣ ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ለሆኑ ግዥዎች የሚወዳደሩ አቅራቢዎች የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ ስለሚሆኑ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ የተጫራቾች መመሪያውንና የእቃዎችን ዝርዝር የሚገልጽ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሰራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 009 ባ/ዳር መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋው 1.5 በመቶ ያላነሰ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ገቢ መደረግ ይኖርባቸል፡፡
  4. የሚገዙ እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊካሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን በማስፈርና በጥንቃቄ በማሸግ ለአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 013 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታተይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት የሚያግድ ነገር አይኖርም፡፡
  7. የርክክብ ቦታ ባ/ዳር ከተማ መ/ቤቱ ድረስ በግንባር በመቅረብ ይሆናል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058 220 19 92 /058 226 27 19 ባ/ዳር ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-19
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታተይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-19 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታተይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Office of Auditor General
  • Bid bond: 1.5%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Nov 09, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T12:44:17.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders