Equipment and Accessories

አማራ ልማት ማህበር (አልማ) ላፕቶፕ፣ ኮምፒውተር እና ታብሌት በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በማወዳደር በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቀስ በትምህርት፣ በጤና እና በሥራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ማህበሩ ከአሜሪካ ዲፓርትመንት ኦፍ ስቴት(US-DO) ባገኘው ድጋፍ የቤተሰብ ተኮር ኤች አይቪ መከላከል፣ እንክብካቤ እና ሕክምና አገልግሎት ፕሮጀክት የሚሆን ላፕቶፕ፣ ኮምፒውተር እና ታብሌት በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በማወዳደር በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የተጨማሪ አሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በመንግስት ግዥ አዲሱ የአቅራቢዎች ዝርዝር መረጃ ላይ ማለት https://www.egp.ppa.gov.et    የተመዘገበ፡፡
  4.  ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሽህ ብር) ብቻ በመክፈል ባሕር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት አንድ ወጥ በሆነ ኢንቨሎፕ ማስጋባት አለባቸው፡፡
  8.  የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ዋናው መ/ ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
  9. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-19
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Bid opening: 2026-11-19 15:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Development Association (ADA)
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published on: Be'kur (Nov 09, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T13:52:59.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders