Equipment and Accessories
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ለተቋሙ መገልገያ የሚሆን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች /ዳሽ ቦርድ እና ታብሌት/፣ የጽሕፈት መሳሪያ /ጃንባ ኬንት/ እና የክብር መዝገብ ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Amhara
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓም
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ለተቋሙ መገልገያ የሚሆን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች /ዳሽ ቦርድ እና ታብሌት/፣ የጽሕፈት መሳሪያ /ጃንባ ኬንት/ እና የክብር መዝገብ ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መ/ቤቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ወይም ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች /ሎቶች/ አንድ በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በግዥና ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሪክቶሬት ቢሮ ቁጥር 07 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በዓል ወይም የሥራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 31 58 ፋክስ 058 320 11 83 ፖ.ሳ.ቁ 965 ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-11-19
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
- Bid opening: 2026-11-19 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Be'kur (Nov 09, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T13:56:27.000Z
- Source: Qelal Tenders