Other Sales
የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የእቅድና ገንዘብ ጽ/ቤት ሮቤ የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል የዳቦ ስንዴ እና ገብስ ዝርያ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ለአንደኛ ጊዜ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/213/2019
የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የእቅድና ገንዘብ ጽ/ቤት ሮቤ የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018 በጋ ወቅት ያመረታቸውን
- የተለያዩ የስንዴ እና ገብስ ዝርያ ብዛት የዳቦ ስንዴ ብዛት በኩንታል 824.10 (ስምንት መቶ ሃያ አራት ኩንታል ከ 10 ኪ.ም) እና
- ገብስ ብዛት በኩንታል 453.12 (አራት መቶ ሀምሳ ሶስት ኩንታል ከ 12ኪ.ም) በማሽን ተበጥረው ንፁህ ለምግብና ለፋብሪካ የሚውሉ የዳቦ ስንዴ እና ገብስ ዝርያ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን እና ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ባለቤቶች ፤መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ ግለሰብ ነጋዴዎች በጨረታው መወዳደር ይችላሎ ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) Oromia Agricultural Research Institute Internal Revenue B ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000466928357 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማስገባት ሰነዱን ከደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የእቅድና ገንዘብ ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 10 መግዛት የሚችሉ ሲሆን ፣ ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የስንዴ ዝርያዎች ዓይነት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20% (20 ፕርሰንት) የያዘ ሲፒኦ ብቻ የሲናና ግብርና ምርምር ማዕከል ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ የሚጫረቱበን ሰነድ በመግዛት ıኛ, አሪጂናል የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ እና 2ኛ ዋጋ የተሞላባት ኮፒ ሰነድ ለሁለቱንም ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት አለት እና ሰአት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ላይ የድርጅታቸውን ወይም የግለሰቡን የነጋዴውን ስም እና ሙሉ አድራሻ ስልክ ቁጥር በመፃፍ መፈረም ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሲናና : ግብርና ምርምር ማዕከል ስም ያስያዙትን ሲፒኦ ኦሪጂናል የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላባት ሰነድ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በእያንዳንዱ የመወዳደሪያ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት።
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የእቅድ እና ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በመክፈል ስንዴውን መረከብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ማዕከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0930292332 ደውለው ይጠይቁ።
የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን
የእቅድና ገንዘብ ጽ/ቤት ሮቤ
Tender details
- Deadline: 2026-11-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-28 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Bale Zone Sinana Agriculture Research Institute
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
- Posted at: 2026-11-11T09:36:56.000Z
- Source: Qelal Tenders