Disposal Sale
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ከምባታ ዞን የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት አገልግሎት የማይሰጡ የቱቡላሬዎችንና ፌሮ ብረቶች በማሰባሰብ በተደራጀ መልኩ በግልጽ ጨረታ በሽያጭ ለማስወገድ ይፈልጋል
Description
አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን ለማስወገድ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ከምባታ ዞን የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት አገልግሎት የማይሰጡ የቱቡላሬዎችንና ፌሮ ብረቶች በማሰባሰብ በተደራጀ መልኩ በግልጽ ጨረታ በሽያጭ ለማስወገድ ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ተጫራቾች፡-
1. ተጫራቾች ለውድድር ሲቀርቡ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
2. የጨረታ ማስከበሪያ 50000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይቻላል፣
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
4. ተጫራቾች ከዋና አስፓልት መንገድ አጥር የተነሱ ቱቡላሬዎችን እና ያገለገሉ ፌሮ ብረቶችን በአዲሱ ማዘገጃ ግቢ በመገኘት በሥራ ሰዓት በአካል ማየት ይችላሉ፣
5. ተጫራቾች የቱቡላሬዎችንና ፌሮ ብረቶች መነሻ ዋጋ በመደበኛ ጨረታ ሠነደ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ከመነሻ ዋጋ በላይ ሞልተው መወዳደር አለበቸው፣
6. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ዋጋን በፖስታ በማሸግ አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ ጨረታው በአየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን እያንዳንዱን ዋጋ ከመነሻ ዋጋ በላይ በመሙላት መወዳደር የሚችል ሆኖ ጨረታው በ16ኛ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሸጎ 9፡00 የሚከፈት ይሆናል። ሆኖም ግን የሚከፈተው ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን መ/ቤቱ በአክብሮት ያሳውቃል።
ማሳሰቢያ፡- ንብረቶቹ ከዋና አስፓልት መንገድ አጥር የተነሱ ቱቡላሬዎች እና ያገለገሉ ፌሮ ብረቶችን በአዲሱ ማዘጋጃ ግቢ ዉስጥ የሚገኝ ስለሆነ ዘውትር በሥራ ቀናት ምልከታ ማድረግ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ፦ +251 94 100 5827 / +251 93 259 1817
በዱራሜ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
Tender details
- Deadline: 2026-11-28
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-28 15:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን 9፡00 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Kembata Tembaro Zone Durame City FEDB
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 13, 2026)
- Posted at: 2026-11-13T08:19:14.000Z
- Source: Qelal Tenders