Other Sales
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ ያገለገሉ የመንግስት ንብረቶች ማለትም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 105 UPS/ዩፒኤስ/ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ መመሪያ (ጨረታ ቁጥር ግ1/2019)
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ ያገለገሉ የመንግስት ንብረቶች ማለትም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 105 UPS/ዩፒኤስ/ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ላይ ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት ቅዳሜን ሳይጨምር ከ7፡00-11፡00 ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ) በመክፈል ከቅ/ጽ/ቤቱ ግቢ በሚገኘው ሀብት አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
1. ማንኛውም በጨረታ የሚሳተፍ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች ለሚወዳደሩበት ምድብ ለዕቃዎች የሰጡት ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) የጨረታ መስከበሪያ ዋስትና የሚሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ በባንክ የተመሰከረ CPO (ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSON MODO BRANCH OFFICE )አካውንት ቁጥር ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከተያያዥ ሰነዶች ጋር ማለትም ከሚወዳደሩበት ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለባቸው።
2. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች የተቀመጠ የመነሻ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ በመሆኑ ተጫራቾች የሚሰጡት የመጫረቻ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት።
3. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ሞጆ ደረቅ ወደብ ሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሚገኘው የንብረት አስተዳደር መጋዘን የሚገኙ ስለሆነ በአካል በመሄድ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ዕቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡ ለሚፈጠረው ችግር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
4. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ሽያጫቸው የሚፈጸመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ መጠየቅ አይችሉም፡፡ ተጫቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቾቹ የሚሰጠው ዋጋ ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ በአኃዝና በፊደል ሆኖ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላት አለባቸው፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለውና ለማየት አጠራጠሪ የሆነ ዋጋ መግለጫ ተቀባይነት የለውም።
5. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ የተጫራች አድራሻ በሚል ቦታ ላይ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ፣ ፊርማቸውን የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከዚህ ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት የለውም።
6. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋት 3፡45 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡የጨረታው ሳጥን በዚህ ቀን 3፡45 ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ደረቅ ወደብ በሚገኘው ቅ/ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ይከፈታል።
7. ከተጠቀሰው የግዜ ገደብ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የለውም።
8. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችሉም።
9. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታው ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ጸንቶ ይቆያል፡፡ የጨረታው ውጤት በቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ከጸደቀ የሽያጭ ውል ተደርጎ ይቆጠራል።
10. ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጨረታውን ለማሸነፍ ሲል መደለያ የሰጠ ወይም ለመስጠት የሞከረ እንደሆነ ከጨረታው ይሰረዛል።
11. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም ቅሬታ ያለው ተጫራች በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለጨረታ ኮሚቴ ሰብሳቢ ማቅረብ ይችላል፡፡ አሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከቅሬታ ማቅረቢያ ቀን በኋላ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ካሸነፉበት ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ይሆናል።
12. አሸናፊ ተጫራቾች የቅሬታ ማቅረቢያ ቀን ካለፈ በኋላ በአስር የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ በመክፈል ዕቃውን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
13. አሸናፊ ተጫራቾች ከላይ በተገለፀው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምንም እንኳን ሙሉ ክፍያውን ቢከፍሉም ነገር ግን ዕቃውን ካላነሱ የተገለጸውን የግዜ ገደብ ካለፈ ቀን ጀምሮ የመጋዘን ኪራይ የሚታሰብ ሆኖ በተጨማሪም በዕቃው ላይ ለሚደርስ ጉዳት ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
14. አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃዎቹን ለመረከብ እና ለመጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ እራሳቸው ይችላሉ።
15. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-116-1589 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-12-02
- Bid closing time: 09:45
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋት 3፡45 ሰዓት
- Bid opening: 2026-12-02 10:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 14, 2026)
- Posted at: 2026-11-14T07:48:13.000Z
- Source: Qelal Tenders