Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉል ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉል

  1. የጽ/መሳሪያ
  2. የፅዳት እቃ
  3. የተለያዩ ህትመቶች
  4. የመብራት ዕቃ
  5. ዉሃ እቃዎች
  6. የቢሮ መገልገያ እቃዎች ፈርኒቸሮች
  7. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  8. የመኪና ጎማ ከነ ከመናዳሪ
  9. የኦክስጅን ሙሌት ከነማጓጓዣ እና ጫኝና አውራጅን ጨምሮ የኦከስጅን ሲሊንደር አጠቃላይ ጥገና ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

በዘመኑ/2019 በጀት ዓመት የታደሰ ወይም አዲስ የወጣ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፈቃድ ያላቸዉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ።

የግዥ መጠኑ 200,00.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ የእለት ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከዚህ በታች በተመለከተው ሰንጠረዥ መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የተከፈለበትን ደረሰኝ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብረው አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

ተ.ቁ

ሎት

የግዥው አይነት

የጨረታ ሰነድ የጨረታ መሸጫ ብር

የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን

ምርመራ

 

1

ሎት-1

የጽ/መሳሪያ

200

40,000

 

2

ሎት_2

የፅዳት እቃ

200

25.000

 

3

ሎት_4

የተለያዩ ህትመቶች

200

20,000

 

4

ሎት_5

የመብራት ዕቃ

200

35,000

 

5

ሎት_6

ዉሃ እቃዎች

200

35,000

 

6

ሎት_7

የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች /ፈርኒቸሮች/

200

20,000

 

7

ሎት_8

ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

200

50,000

 

8

ሎት_9

የመኪና ጎማ

200

25,000

 

9

ሎት-11

 

የኦክስጅን ሙሌት ከነማጓጓዣ እና ጫኝና አውራጅን ጨምሮ የኦክስጅን ሲሊንደር አጠቃላይ ጥገና

200

40,000

 

 

  • ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
  • ሁሉም ተጫራቾች በእያንዳንዱ የሥራ ዝርዝርና የተጫራቾች መመሪያ መሰረት የመፈፀም ግዴታ አለባቸዉ።
  • ተጫራቾች ለሚሳተፉበት ጨረታ ህጋዊና ተቀባይነት እና አግባብነት ያለዉ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸዉ።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸዉን ጨረታዎች በሆስፒታሉ የጨረታ ሰነድ አይነትና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን/ መሰረት ማቅረብ አለባቸዉ። ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ የተመረተበትን አገርና ብራንድ መጥቀስ አለባቸዉ።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ጥራት ያለዉና አንደኛ ደረጃ ሆኖ በገበያ ላይ ተመራጭነት ያለዉ መሆን አለበት።
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ከማቅረባቸዉ በፊት ናሙና በማቅረብ ትክክለኛነቱ ከተረጋገጠ በኋላ በራሳቸዉ ወጭ በማቅረብ ለሆስፒታሉ ንብረት ክፍል ማስረከብ አለባቸዉ። ሆስፒታሉ የእቃዉን ጥራትና በናሙናዉ መሰረት የቀረበ መሆኑን በሚመለከታቸዉ ባለሞያዎችና ሃላፊዎች በማረጋገጥ ይረከባል። ተጫራቾች የሚታተሙ ህትመቶችን በሆስፒታሉ ናሙና መሰረት ሰርተዉ ማቅረብ አለባቸዉ። ተጫራቾች ሆስፒታሉ አለባቸው።
  • ከአሁን በፊት ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው መሆን ተጫራቾች በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ የቀረቡትን እቃዎች በሙሉ ዋጋ መሙላት አለባቸዉ።
  • ተጫራቾች ሆስፒታሉ ካቀረበው ዝርዝር ዋጋ ማቅረቢያ ውጭ በሌላ ዋጋ ማቅረቢያ ማቅረብ አይችሉም።
  • የጨረታ ሰነዱንም ለሌላ ማስተላለፍ አይቻልም።
  • በጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ዉጭ ይሆናል።
  • በጨረታ ማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል። ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ አይነት ባሸነፉበት ጥራትና ዋጋ ዝርዝር መሰረት ልዩነት ቢኖረዉና የጥራት ችግር ሲከሰት በራሳቸዉ ውጭ እንደገና የመተካት እና የማቅረብ ግዴታ አለባቸዉ። ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ናሙና ሳያቀርቡ ሙሉ ለሙሉ ይዘዉ ቢመጡና እቃዉ ተፈላጊ አይነት ሳይሆን ቢቀር ሙሉ ለሙሉ ወዲያዉኑ መልሰዉ በራሳቸዉ ወጭ ናሙና አቅርበዉ በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ካሸነፉ በኋላ ያሽንፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ፣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው።ተጫራቾች አሸናፊነታቸዉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ዉስጥ የዉል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ በዉልና ማስረጃ ዉለታ በመፈፀም ማቅረብ አለባቸዉ ለ10 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይችላሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የጨረታ ሳጥኑ ወዲያዉኑ ይታሸጋል በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ይከፈታል። በአላት ቀን ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል። የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ40ቀን ፀንቶ ይቆያል።
  • ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር 011 681 3390 ወይም በፋክስ 011 681 1008 ቁጥር በመላክ መጠየቅ ይቻላል።

መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ይሁን በሙሉ የመሠረዝ መብቱ እንዲሁም ግዥዉን በጥቅል ወይም በተናጠል አወዳድሮ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-26 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debrebirhan Specialized Hospital
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T12:09:17.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders