Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በምዕ/ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ የተለያዩ ጨረታዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕ/ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ የተለያዩ ጨረታዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ሎት 1. የጽህፈትና የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 2. የመኪና ጎማና መለዋወጫ፣ ሎት 3. የደንብ ልብስ፣ ሎት 4. የተለያዩ ሶፍትዌሮችን፣ ሎት 5. መጋረጃና ምንጣፍ፣ ሎት 6. ኤሌክትሮኒክስና ተዛማች እቃዎች ሎት 7. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 8. የዱቄት ፋብሪካ መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 9. የደረሰኝ ህትመት ሎት 10. የእርሻ መሳሪያ መለዋወጫ መግዛት  ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ ያላቸዉ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።

2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው።

3.  የጨረታው ዋጋ 200.000  (ከሁለት መቶ ሽህ  ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማስያዝ እና የሚሞሉት ዋጋ የቫት የግብይት ከሆነ ከነቫቱ መሆን አለበት፡፡

4.  ከላይ የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 205 ሂሳብ ክፍል/ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 11 የስራ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን እና በዚሁ ቀን ማለትም በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡

6.  የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡

7.  ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡

8. ተጫራቾች በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማያያዝ አለባቸው፡፡

9. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስገባት ውል መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡ እንዲሁም አሸናፊ አካል ህጋዊ የሆነ ኪ አር ኮድ ደረሰኝ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

12. የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ 03 ቀበሌ ከሚገኘው ዋና ቢሮ ይሆናል፡፡

13. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40/ 09 00 31 81 07 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- የመክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀንና ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኔዬን ኃ.የ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 11 የስራ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00
  • Bid opening: 2026-11-26 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 11 የስራ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Damot United Work Union
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T13:48:04.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders