Stationery
በአብክመ በምስ/ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ ፅህፈት መሳሪያ፣ ሌሎች አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሳተም ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በምስ/ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2. ሌሎች አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት 4. ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሳተም ይፈልጋል፡፡
የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላ ላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሃሳባቸውን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣበት በመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10 ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት አስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በ11ኛው ቀን 4፡15 ሰዓት ላይ ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሠነዱን ቢሮ ቁጥር 7 200‚000 (ሁለት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል መውሠድ ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ሰፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 66 10 002 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የሚገዙትን እቃዎች 20 በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አሸናፊው ተቋሙ ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎቱ ወይም በጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ500 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያው ያልተዘረዘሩት ህጎች ሁሉ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 144/2018 ተግባራዊ ይሆናል፡፡
የሞጣ ከተማ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣበት በመጀመሪያ ቀን አንስቶ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-26 10:15
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣበት በመጀመሪያ ቀን አንስቶ 11ኛው ቀን 4፡15 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Mota Health Post
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T13:50:24.000Z
- Source: Qelal Tenders