Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የሐይቅ ማረሚያ ቤት አስ/ር ጽ/ቤት የ2019  በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የሐይቅ ማረሚያ ቤት አስ/ር ጽ/ቤት የ2019  በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎችን፤ የቢሮ ወንበሮች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የቢሮ መገልገያዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ፕሪንትር፣ ፕሪንተርና ኮምፒውተር እንዲሁም ጀኔሬተር ጥገና፣ የመኪና ጎማ እና ለህግ ታራሚዎች የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ማለትም ቀይ ጤፍ፣ ቀይ ማሽላ፣ ነጭ በቆሎ፣ ዛላ በርበሬ፣ የምግብ ጨዉ፣ ጎመን ዘር እና የመሳሰሉትን ለምግብና አስፈላጊ ናቸዉ የተባሉትን ግብዓቶችን ከታህሳስ እስከ ግንቦት ወር የሚያስፈልጋቸውን ግብዓት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. በዘርፉ ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

3. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡

4. የግዥ መጠን ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዬን ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ የእቃውን ወይም የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዙበትን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፤ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500  (አምስት መቶ ብር)  በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሐይቅ ማረሚያ ቤት አስ/ር ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ወይም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት 07/03/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/03/2019 ዓ.ም ድረስ ማስገባት አለበት፡፡

9. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 4 በ11ኛው ቀን 17/03/2019 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው መከፈት አይስተጓጎልም፣ የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድና ቅዳሜ እንዲሁም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን በተቀመጠው ስዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 222 05 80/17 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

12. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀና በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ካሸነፉት  እቃ ወይም አገልግሎት ጠ/ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለሐይቅ ማረሚያ ቤት አስ/ር ጽ/ቤት አስይዘው ውል በመፈጸም ያሸነፉትን ዕቃ ሐይቅ ማረሚያ ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማስረከብ እያለብዎት ውል ሳይወስዱና ንብረቱን ለማስረከብ ፈቃደኛ ሆነው ካልተገኙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ መሆኑን እንድታውቁና ንብረቱን በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት በተሰጠዎት ጊዜ ውስጥ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

የሐይቅ ማረሚያ ቤት አስ/ር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-26 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: South Wello zone correctional Facility Command Hayek Prison Administration Office
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T13:53:17.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders