Stationery
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ መሬት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ መሬት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2. የስፖርት ትጥቅ፣
- ሎት 3. የደንብ ልብስ፣
- ሎት 4. የደንብ ልብስ ጫማ፣
- ሎት 5. የመኪና መለዋወጫ እንዲሁም
- ሎት 6 የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 7/2019 እስከ ህዳር 17/2019 ዓ.ም የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 26 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የጠ/ድምር ሎት 1. ብር 20,000፣ ሎት 2. ብር 25,000፣ ሎት 3. ብር 15,000፣ ሎት ብር 415,000፣ ሎት 5. ብር 10,000፣ ሎት 6. ብር 13,500 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከዋና ገ/ያዥ በደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ2 ኮፒ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ኦርጅናል ሰነዱ ውስጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ቢሮ ቁጥር 35 የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ህዳር 17/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 18/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ቢኖሩም ባይኖሩም ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የጨረታ ውጤቱን በጠቅላላ ድምር ውጤት ያያል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን ደ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 34 በራሱ ትራንስፓርት ማቅርብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 20,000 (ሀያ ሸህ ብር) በላይ ከሆነ 3 በመቶ ታክስ መክፈል አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የእቃዎችን ጥራት በተመለከተ ለሚከለከታቸው ባለሙያዎች ጥራቱን በማረጋገጥ ማስረከብ ግዴታው ነው፡፡ በጥራት አረጋጋጭ ባለሙያ መስረት የጥራት ችግር ያለባቸው ሙሉ በሙሉ በመመለስ ትክክለኛ ጥራት ያላቸውን እቃዎች የማቅርብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 35 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 117 00 86 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ሰነዱ ሲሞላ የዘመኑ የግብር የከፈሉ መሆኑን ክሊራንስ እና የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ማቅርብ አለባቸው፡፡ ስርዝ ድልዝ እና ፓራፍ ማድረግ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደረጋል በጥንቃቄ ተሞልቶ መቅረብ ይኖረበታል፡፡
የደባርቅ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-27 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Debark City Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T13:56:13.000Z
- Source: Qelal Tenders