Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በምስ/ጐጃም ዞን የስናን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለባለበጀት ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስ/ጐጃም ዞን የስናን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለባለበጀት ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት 1. የጽ/መሳሪያዎች፣ ሎት 2. ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 3. የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት 4. የውጭ ስሪት ፈርኒቸር፣ ሎት 5. ህትመት፣ ሎት 6. የጽዳት እቃ፣ ሎት 7. ጫማ፣ ሎት 8. የተዘጋጁ አልባሳት፣ ሎት 9. ብትን ጨርቅ፣ ሎት 10. ጄኔሬተር፣ ሎት 11. ኤሌክትሪክ እቃ፣ ሎት 12. የኮንስትራክሽን እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
1. በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ምዝገባ ያላቸው፡፡
3. ከ500 ሽህ ብር በላይ ለሆኑ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተወዳዳሪዎች በግብር አመቱ ተገቢውን የታክስ እና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የሚገዙ እቃዎችን መጠንና ዝርዝር መግለጫ ከሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሎት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ስናን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ የግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ለሎት 1. ብር 15,000፣ ለሎት 2. ብር 10,000፣ ለሎት 3. ብር 5,000፣ ለሎት 4. ብር 5,000፣ ለሎት 5. ብር 3,000፣ ለሎት 6. ብር 3,000፣ ሎት 7. ብር 10,000፣ ሎት 8. ብር 10,000፣ ሎት 9. ብር 10,000 ፣ሎት 10. ብር 5,000፣ ሎት 11. ብር 3,000፣ ሎት 12. ብር 8,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
9. ተጫራቾች በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅ ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙትን ሲፒኦ ወይም ደረሰኝ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ሶስቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ የመ/ቤቱን እና የአቅራቢውን ስምና አድራሻ በመጻፍ በማህተምና ፊርማ አስደግፎ ስናን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
10. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 3፡30 ድረስ በማስገባት በዚህ ቀን ጨረታው ላይ ለመገኘት ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙም) ቢሮ ቁጥር 04 ከጠዋቱ 4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
11. የጨረታው አሸናፊ የአሸነፉባቸውን እቃዎች ስናን ወረዳ በግዥ ጠያቂ መ/ቤቶች ንብረት ከፍል አምጥቶ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
14. መ/ቤቱ የሚያወዳድረው በሎት ነው፡፡
15. በርክክብ ወቅት ለተጠቃሚው መስሪያ ቤት ጥራታቸውን ማሳየት ይኖርባቸዋል።
16. ናሙና የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች በናሙናው መሰረት ይቀርባል፡፡
17. ነጠላ ዋጋው ላይም ሆነ ጠቅላላ ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
ማሣሠቢያ፡- የጨረታ መክፈቻ ቀን የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ስዓት ይከፈታል፡፡
አድራሻ ከደ/ማርቆስ ከተማ በ27 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንገኛለን።
የስናን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-26
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በ11ኛው ቀን 3፡30
- Bid opening: 2026-11-26 10:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: East Gojam Zone Sinan Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Buyer's registered address: ከደ/ማርቆስ 27 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ረ/ገበያ ከተማ ነዉ፡፡
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T14:00:00.000Z
- Source: Qelal Tenders