Textile, Garment and Leather
በደቡብ ወሎ ዞን የንግስት ዘዉዲቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የህትመት ሥራ እና የጽዳት ዕቃዎች ማወዳደር ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ወሎ ዞን የንግስት ዘዉዲቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
- ሎት 1. የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 3. የህትመት ሥራ እና
- ሎት 4. የጽዳት ዕቃዎች ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ዉድድሩ የሚካሄደዉ በሎት ነዉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ለየብቻ በጥንቃቄ አሽገዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በደቡብ ወሎ ዞን ከንግስት ዘዉዲቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ዉስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች መካከል ከፋፍለው መጫረት አይቻልም ሆኖም በሎት ዉስጥ ከተዘረዘሩት እቃዎች ዉስጥ አንድ የዕቃ ዋጋ ሳይሰጥበት ቢቀር ተጫራቹ ድርጅት ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የሎት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋዉን ቫቱን ጨምሮ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ተወደድሮ ባሸነፈበት ዝርዝር ጥቅል ዋጋ መሰረት የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም በሎቱ ዉስጥ ከተዘረዘሩት እቃዎች ዉስጥ አንድም እቃዎች ማቅረብ ባይችሉ ያስያዙት 10 በመቶ ሙሉዉን የዉል ማስከበሪያ ብር ወደ መንግስት ገቢ የሚሆን ይሆናል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11ኛዉ ቀን ከሰዓት 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ በንግስት ዘዉዲቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በዚያዉ 11ኛዉ ቀን 8፡30 ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻዉ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ የጨረታ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 14 06 75 89 /09 20 47 95 28 /09 14 33 01 95 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የንግስት ዘዉዲቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
ወረኢሉ
Tender details
- Deadline: 2026-11-26
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛዉ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-26 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛዉ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Nigist Zewuditu Elementary Hospital
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T14:01:26.000Z
- Source: Qelal Tenders