Stationery

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች (ሎት 1)፣ ዓመታዊ የመኪኖች ኢንሹራንስ (ሎት 2) እና የእንስሳት መድኃኒት (ሎት 3) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ የጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት ለሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  •  ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ፣
  • ሎት 2. የዓመታዊ የመኪኖች ኢንሹራንስ እና
  • ሎት 3. የእንስሳት መድሃኒት

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል መያዝና መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3.  የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማለትም የንግድ ፈቃድ፣ ቲን ሰርተፊኬት፣ የታክስ ክሊራንስ፣
    የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ወይም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ጨረታ ከወጣበት ከህዳር 07/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ህዳር 16/2019 ዓ/ም በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፡፡
  6.  ጨረታ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ድምር ነው፡፡ ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ በሎት 1. ብር 10,000 (አሰር ሽህ ብር) እና በሎት 2. ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) ብቻ ሎት 3. ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ፣ ሲፒኦ፣ (ቢድ ቦንድ) ወይም በጥሬ ገንዘብ መ/ቤታችን በመሂ 1 ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ ጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከህዳር 7/2019 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት እስከ 16/2019 ዓ/ም እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጓ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ህዳር 17/2019 ዓ/ም የጨረታ ሳጥኑ ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ተጫራቾች ግን በዕለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ድርጅቱ ህጋዊ የንግድ ማህተም እና ፊርማ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  13. የሞሉትን ዋጋ ለ45 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  14. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 225 05 06 /058 225 00 09 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 የጓንጓ ወረዳ ገንዘብ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-26 10:15
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Guangua Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T14:07:19.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders