Land Lease & Real Estate

በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስ/መሬት ጽ/ቤት ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ 12 ቦታዎችን በመደበኛ የከተማ ቦታ ሊዝ ጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስ/መሬት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 መሰረት ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ 12 ቦታዎችን በመደበኛ የከተማ ቦታ ሊዝ ጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በሊዝ መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400 (አራት መቶ) ብር በመክፈል አማኑኤል ከተማ አስ/መሬት ጽ/ቤት በመቅረብ ሰነድ መግዛት እና መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪው የስራ ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡

2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚያበቃው ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከታተመበት እስከ 10 የስራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ላይ ይሆናል፡፡

3. የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት በ10 የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ላይ ይሆናል፡፡

4. ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎች የጉብኝት ፕሮግራም በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ይሆናል፡፡

5. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ላይ በአማኑኤል ከተማ አስ/መሬት ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት በ11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

6. ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአማኑኤል ከተማ አስ/መሬት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት በ10 የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00
  • Bid opening: 2026-11-27 09:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የአማኑኤል ከተማ አስ/መሬት ጽ/ቤት
  • Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T14:11:23.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders