Stationery
የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች እና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በበጀት አመቱ ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ምድብ 1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ምድብ 2. የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የነጋዴዎች መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን ሰነዶች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግዥ ላይ ተሳትፈው በውለታቸው መሰረት ባለማቅረባቸው ምክንያት ስልጣን ባለው አካል እገዳ ያልተደረገባቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠ/ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ የአንድ እቃ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ለይተው መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ የሞሉትን ሰነድ ኦርጂናልና ኮፒ ብለው በመለየት በተለያዩ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ማስረጃቸውን በተለየ ፖስታ በማሸግ ስምና አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር ከላይ በመፃፍ ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ በትልቅ ፖስታ በጥንቃቄ በማሽግ ቢሮ ቁጥር 43 ፊት ለፊት በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ኛው ቀን እስከ 11፡30 ይቆይና በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አይስተጓጉልም፡፡
- በዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን እቃዎች በፍ/ሰላም ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ካለው ንብረት ክፍል አምጥተው የሚያስረክቡ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን ሲሞሉ የጨረታ ሰነዱ በሚያስቀምጠው አይነትና ዝርዝር መግለጫ መሰረት ብቻ ተሞልቶ መቅረብ አለበት፡፡
- ሁሉም ተጫራች የዋጋ መሙያ ላይ ዋጋ ሲሞላ በአጠቃላይ እቃዎችን ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ምክንያቱም አሸናፊ የሚለየው ጽ/ቤቱ በመረጠው በሎት ወይም በተናጠል የሚታይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፍ/ከተ/አስ/ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 43 ከዋና ገንዘብ ያዥ እጅ የማይመለስ ለሁሉም ሎቶች ብር 200 ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ የጨረታ ሰነድ ያልተጠቀሱ ለዚህ ጨረታ የሚያስፈልጉ ነጥቦች ሀምሌ/2018 በተሻሻለው የግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 43 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 16 29 /883 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-26
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-26 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Finote Selam City Adminstaration F/E/D/Bureau
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T14:13:02.000Z
- Source: Qelal Tenders