Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የምስራቅ ጎጃም ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ጎጃም ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2. የጽዳት እቃ፣
- ሎት 3. ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን 500‚000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚያሳትፍ፣ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት የተመዘገቡና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ በመሂ 1፣ በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከየጁቤ የመ/ደ/ሆስፒታል የግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰዱን በአንድ ፖስታ በማሸግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለባሶ ሊበን ወረዳ የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 በግልጽ ይከፈታል፤ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ለመክፈት የማያግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም አለበት፡፡ በተገለፀው የጊዜ ገደብ ያልቀረበ እና ውል ያልፈጸመ እንደሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ መ/ቤቱ ውርስ ያደርጋል።
- ውድድሩ በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ የሚለይ በመሆኑ ተጫራቾች ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ያሸነፈበትን እቃ ኦርጅናል እቃዎችን የጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ መሙያው ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለም ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- ሆስፒታሉ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 246 0274 በመደወል ማግኘት፡፡
የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-12-01
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-12-01 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T14:20:59.000Z
- Source: Qelal Tenders