የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ሁለት ሞተር ሳይክሎች በጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ሁለት ሞተር ሳይክሎች በጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ለመሸጥ ይፈልጋል።

ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በድርጅቱ የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000175714468 በማስገባት የባንክ ስሊፕ ይዞ ስታዲየም ፊት ለፊት ወጋገን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ጎን ዳሸን ባንክ በሚገኝበት ሳህለ ሥላሴ ህንጻ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 በሚገኘው ዋና መስሪያ በመምጣት እና ሰነዱን በመግዛት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን። ለውሳኔ ይረዳችሁ ዘንድ የሞተሮቹን ለማየት አዲስ አበባ መስቀል ፍላወር ጆርጂያ ኢምባሲ ፊት ለፊት እና ሐረር ከተማ ሐረር ቀጠና ቴሌ ጐን በአካል በመገኘት ከሚያዝያ 20 እስከ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 3 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ጨረታው ከሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓም እስከ ሚያዝያ 26 ቀን ዓ.ም የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፤

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የመጨረሻው ቀን ከቀኑ 9፡30 በኢሰመጉ ዋናው መስሪያ ቤት ይሆናል።

.

የተሸከርካሪው ዓይነት

የተሰራበት ዘመን

ቀለም

 

ሞዴል ቁጥሩ 

የሻንሲ ቁጥሩ

 

ሞተር ቁጥሩ

 

1

Red fox ሞተር ሳይክል

2002

ቀይ

RF175-8

 

LY4YCCNCX9K004141

YG163FMK99000141

2

Red fox ሞተር ሳይክል

2002

ቀይ

RF175-8

L4YCCNC59k004161

 

YG163FMK99000161

 

ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸው ሁኔታዎች

  1. የጨረታው ሰነድ ድርጅቱ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መግባት የሚገባው በታሸገ ፖስታ ታሽጎ ነው፣

2. ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ግለሰቡ ወይም ህጋዊ ወኪል መገኘት የሚኖርበት ሲሆን፤ ያልተገኘ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፣

3. ማንኛውም የጨረታ ዶክመንት ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ ቢመጣ ተቀባይነት አይኖረውም፣

4. በቀረበው የጨረታ ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፣

5. ተጫራቾች ለተጫረቱት የሞተር ሳይክል የመነሻውን ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የባንክ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

6. ሌሎች ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፤

7. ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማንኛውንም ወጪ ሙሉ በሙሉ የሚሸፍነው ገዢው ነው፣

8. በጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ሙሉ ስም፣ የመኖሪያ አድራሻ፣ ከፍለ ከተማ፣ ወረዳ፣ የቤት ቁጥር፣ ስልክ ቁጥር እና ፊርማ በግልጽ መቀመጥ አለበት፣ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንም ተጫራች ዋጋ መለወጥም ሆነ ማሻሻል አይችልም፡፡

9, የጨረታው አሸናፊ አሸናፊዎች ማሸነፉ ከድርጅቱ በግልጽ ደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን መረከብ እና ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለበት አለባቸው። ይህ ካልሆነ ባሸነፉበት ዋጋ ሁለተኛ አሸናፊ ከተስማሙ እንዲወስዱ ተደርጎ የመጀመሪያው አሸናፊ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።

10 በጨረታው አሸናፊ ላልሆኑት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ተመላሽ ይደረግላቸዋል፤

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-

ስታዲየም ፊት ለፊት ወጋገን ባንክ ዋና መስራያ ቤት አጠጉብ ዳሸን ባንክ በሚገኝበት ሳህለ ሥላሴ ህንጻ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19

ስልክ ቁጥር፡- 251 90 159 4327

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)


Tender details

  • Deadline: 2026-05-04
  • Bid closing time: 15:30
  • Bid closing (note): ከሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓም እስከ ሚያዝያ 26 ቀን ዓ.ም
  • Bid opening: 2026-05-04 15:30
  • Bid opening (note): ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የመጨረሻው ቀን ከቀኑ 9፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COUNCIL
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 23, 2026
  • Posted at: 2026-04-23T08:20:14.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders