ሕብረት ኢንሹራንስ ለደንበኞቹ የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች፣ የኩባንያው ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካል ቅሪቶችንና በተለያዩ ምክንያቶች ደንበኞች ያልተረከቡዋቸውን ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ሕብረት ኢንሹራንስ ለደንበኞቹ የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች፣ የኩባንያው ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች፣ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካል ቅሪቶችንና በተለያዩ ምክንያቶች ደንበኞች ያልተረከቡዋቸውን ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ቁጥር 73
ክፍል 1 የተጫራቾች መመሪያ
1.1. ተጫራቾች ቃሊቲ ጂቲ ኪዳነ ምህረት ፊት ለፊት ዲ.ኤች ገዳ ብርድልብስ ፋብሪካ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያው የተጎዱ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ንብረቶች ማቆያ (ሪከቨሪ) ከሚያዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሥራ ሰዓት በመምጣት ተሽከርካሪዎችንና ሌሎች ንብረቶችን ማየት ይችላሉ። እንዲሁም የእረፍትና የበአል ቀናትን ጨምሮ በተለመደው የስራ ሰዓት መመልከት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን።
1.2. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ወይም ሌሎች ንብረቶችን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ሰዓት ድረስ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
1.3. ተጫራቾች ለተሽከርካሪዎቹ በዚህ ጨረታ ሰነድ ክፍል ሁለት በተገለፀው መሠረት ለሕብረት ኢንሹራንስ /Hibert Insurance/ ተብሎ በሲፒኦ የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በጨረታው ለተሸነፉ ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል። አሸናፊዎች በጨረታው ላሸነፉት ንብረት ቀሪውን ክፍያ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል።
1.4. የጨረታ አሸናፊዎች የተሽከርካሪዎችን ወይም ሌሎች ንብረቶችን ሙሉ ክፍያ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ጨምረው ከከፈሉ በኋላ ተሽከርካሪዎችን ወይም ሌሎች ንብረቶችን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያሸነፉትን ንብረት ከፍለው ካልወሰዱ ኩባንያው አሸናፊውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ከመሆኑም በላይ ንብረቶቹን ጨረታ በማውጣትም ሆነ ያለጨረታ የመሸጥ፣ የተሸጠበትን ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም።
1.5. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጋር ከከፈሉ በኋላ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪውን ወይም ንብረቶቹን የማያነሱ ከሆነ ኩባንያው ንብረቶቹ ለቆዩበትና ለተጠበቁበት ለእያንዳንዱ ቀን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ያስከፍላል።
1.6. ተሽከርካሪዎች በጨረታ እስከ ተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር ጨረታውን አሸንፈው የሚገዙት ተጫራቾች አይጠየቁበትም። ተሽከርካሪዎቹ ከተሸጡ በኋላ በመንግስት የሚፈለግ የክፍያ ጥያቄ ቢኖር የመክፈል ኃላፊነቱ የገዥው ይሆናል።
1.7. ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችን ኩባንያው ለገዢዎች የሚያስረክበው ገዢዎች በቅድሚያ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሚወስነውን የቀረጥና ታክስ ክፍያ ከፍለው ተገቢውን ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ይሆናል።
1.8. ገዥዎች ተሽከርካሪዎችን ከገዙና ከተረከቡ በኋላ ከክልሎች የሚመጡ ፋይሎችና ክሊራንሶች ቢኖሩ ተከታትለው የሚያመጡት ገዢዎች ይሆናሉ።
1.9. ተጫራቾች ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ከተረከቡ በኋላ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ የስም ዝውውር ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል። ከ6 ወር በኋላ ከስም ዝውውር ጋር በተያያዘ ለሚቀርቡ ጥያቄዎችና ችግሮች ኩባንያው ሃላፊነት አይወስድም።
1.10. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የተሽከርካሪ አገልግሎት አሰጣጥና ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር 19/2010 መሠረት በሚለወጥ ሻንሲ የተባሉ ተሽከርካሪዎች ሻንሲያቸው ካልተለወጠ ኩባንያችን ስም ማዘዋወር የማይችል መሆኑን እንገልፃለን።
1.11. ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል:: ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-05-15
- Publishing entity: United Insurance Company S.C.
- Published: Apr 26, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.