ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ የመኪና ዕቃ መለዋወጫዎች/VEHICLE SPARE PARTS/፣ የህትመት ሥራዎች እና ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ላይ የሚውል የሆስፒታል ደረጃ ያለው የእጅ ማድረቂያ መግዛት እንዲሁም ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እና የመኪና ጎማዎችን በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ
አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን አዋለጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፤ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዘን በሚገኘው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ አትዮጵያ ቀጥሎ በተዘረዘሩት ምድቦች አስቸኳይ ግዢ በሚፈፅምባቸው ልዩ ልዩ መገልገያዎች ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችን በዚህ ማስታወቂያ ይጋብዛል፡-

ምድብ ሀ:- ልዩ ልዩ የመኪና ዕቃ መለዋወጫዎች/VEHICLE SPARE PARIS/፣

ምድብ ለ፦ የህትመት ሥራዎች፤

ምድብ ሐ፦ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ላይ የሚውል የሆስፒታል ደረጃ ያለው የእጅ ማድረቂያ፣

ተጫራቾች ከላይ ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዳቸው ምድቦች የተዘጋጁትን ሰነዶች የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ:: የሦስቱም ምድቦች ጨረታ እስከ አርብ ሰኔ 5፣ 2018ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማብቂያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።

በተጨማሪም ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በሰባት/07/ ምድቦች የተለዩ፣ አገልግሎት ላይ ውለው የሚወገዱ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እና የመኪና ጎማዎችን በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ስለሚፈልግ።

ፍላጎቱ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች ይህ ጨረታ በሪፖርተር የአማርኛው ዕትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት/07/ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 4:00 ሰዐት አስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ታጠቅ የኢንዱስትሪ መንደር በሚገኘው የደስታ መንደር የመልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል በአካል በመገኘት ለቀረቡት ለአንዱ ወይንም እንደፍላጎታቸው ከአንድ በላይ ምድቦች ለየብቻ መወዳደሪያ ዋጋቸውን እስከ ዕረቡ ሰኔ 3፣ 2018 ጠዋት 4፡00 ድረስ እንዲያስገቡ እየጠየቅን፣ ጨረታው በዛው ቀን ሰኔ 3፣ 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

ከላይ የተዘረዘሩትን የጨረታ ምድቦች በከፊል ወይንም በሙሉ ለመሰረዝ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር +251-113716544/45/46 - የውስጥ መስመር 139/182


Tender details

  • Deadline: 2026-06-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-06-12 14:30
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hamlin Fistula Ethiopia
  • Buyer address: Kolfe Keranyo Sub city woreda 09, House number 920 Betel Hospital Street behind Augusta Shirt Factory
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: May 31, 2026
  • Posted at: 2026-06-02T09:14:55.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders