ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ የግንባታ፣ የመደበኛ፤ የሳኒተሪ፣ የኤሌክትሪክ፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፤ የማሽንና ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ጎማና ባትሪ እና የፈርኒቸር እቃዎችን ባህርዳር ዋናው ቢሮ በሚገኙ መጋዝኖች ባህር ዳርና አካባቢው በሚገኙ ፕሮጀክቶች እና ጎንደር ከሚገኘው ከፍ/ፍ/ቤት መጋዘን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ዕቃዎቹ ያሉበትን ሁኔታና አይነታቸውን በአካል ተገኝቶ መመልከት ይቻላል። በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ተወዳዳሪዎች፡-
1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም /unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
3. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ የድሮው አማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የአሁኑ የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናት በመቁጠር) ብቻ ባ/ዳር ከተማ በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 1 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደዉ መንገድ በሚገኘው የድርጅቱ ህንፃ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በ15ኛው ቀን በተገለጸዉ ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ የመዝጊያና መከፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚያኑ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል።
6. ዝርዝር የጨረታ መመሪያውን እና የውል ይዘቱን እንዲሁም የሚሸጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በሙሉ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለበት።
7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 05-82-18-10-04/0912783066/0918 715 641
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-06-23
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-23 14:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Jun 09, 2026
- Posted at: 2026-06-09T09:22:38.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.