የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልፅ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ከቀን 05/10/2018 ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ ቤቱ ይገልፃል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች -
1. የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ
2. ለሀራጅ ጨረታው ለእያንዳንዱ መኪና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ማስያዝ የሚችል፤
3. ግልፅ ጨረታ በመሳተፍ ተሸከርካሪውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
4. ተጫራቹ ለሃራጅ ጨረታ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
5 በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመነሳት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
6. ተጫራቹ በጨረታ አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ ሆነ አለበት፤
7. ተሽከርካሪው አሽንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በመንግስት ገቢ ይሆናል፤
8. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
10. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሲሠጣቸው ይችላል።
11. ተጫራቹ ተሽከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም
12. ተጫራች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ስነድ ከቀን 05/10/2018 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው 09/10/2018 ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
13. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው በቀን 09/10/2018 ከጠዋቱ 4፡15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል
NB-
አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ መኪናውን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
የሻንሲስና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያመጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-16
- Publishing entity: Ethiopian Revenue and Custom Commission Jigjiga Branch Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: Jun 11, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.