Vehicle and Machinery Foreclosure
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት 12 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ ኢሎአ/ያንአኮ/01/2019
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በባለቤትነት የያዛቸውን ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን 12 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪ ዓይነት |
ሞዴል (Model) |
የተመረተበት ዓ.ም (G.C. |
የሰሌዳ ታርጋ ቁጥር (plate no) |
የተሰጠው ኮድ |
የመነሻ ዋጋ |
የጨረታ ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 20% |
|
1 |
ግሬትዎል ፒካፕ |
CC1031PS60 |
2011 |
4-17204 አ.ት |
ELS-01-GW |
1,160,082.08 |
232,016.45 |
|
2 |
ግሬትዎል ፒካፕ |
CC1031PS60 |
2011 |
4-17205 አ.ት |
ELS-02-GW |
1,160,082.08 |
232,016.45 |
|
3 |
ግሬትዎል ፒካፕ |
CC1031PS60 |
2011 |
4-17206 አ.ት |
ELS-03-GW |
1,160,082.08 |
232,016.45 |
|
4 |
ግሬትዎል ፒካፕ |
CC1031PS60 |
2011 |
4-17230 አ.ት |
ELS-04-GW |
1,160,082.08 |
232,016.45 |
|
5 |
ፎርላንድ የጭነት መኪና |
BJ1043V8JE6-2 |
2013 |
4-19447 አ.ት |
ELS-05-FL |
545,318.89 |
109,063.80 |
|
6 |
ፎርላንድ የጭነት መኪና |
BJ1043V8JE6-2 |
2013 |
4-19448 አ.ት |
ELS-06-FL |
621,463.31 |
124,292.70 |
|
7 |
ፎርላንድ የጭነት መኪና |
BJ1043V8JE6-2 |
2010 |
4-17530 አ.ት |
ELS-07-FL |
448,672.91 |
89,734.60 |
|
8 |
ሚስቲቡሽ ፒካፕ |
K77T7ENSL |
2005 |
4-11133 አ.ት |
ELS-08-MP |
526,463.02 |
105,292.65 |
|
9 |
ቶዮታ ሚኒባስ |
YH60LB-JR |
1984 |
4-01665 አ.ት |
ELS-09-TM |
25,508.73 |
5,101.75 |
|
10 |
ጂሊ የቤትአውቶሞቢል |
JL7100A1U |
2007 |
4-40039 አ.ት |
ELS-10-GL |
322,367.49 |
64,473.50 |
|
11 |
ሊፋን 520 የቤት አውቶሞቢል |
LF7130A |
2011 |
4-46001 አ.ት |
ELS-11-LA |
404,122.74 |
80,824.55 |
|
12 |
አባይ የቤት አውቶሞቢል |
HFC7130AG3 |
2009 |
4-46002 አ.ት |
ELS-12-AB |
391,203.21 |
78,240.65 |
- የተሽከርካሪ ምልከታ
ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ከመስከረም 14/2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 20/2019 ዓ.ም ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ ፒያሳ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ጎን በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት ዘወትር በሥራ ቀናት ጠዋት ከ3፡00 እስከ 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 እስከ 10፡30 መመልከት ይችላሉ።
የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ሁሉ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ እስከ 8፡00 (ስምንት ሰዓት) ድረስ ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ሥም በተከፈተው የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግ ዋናውን የባንክ ገቢ ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 31 በአካል ቀርበው በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ከላይ በሰንጠረዡ የተጠቀሰውን የእያንዳንዱ ተሽከርካሪ መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ (unconditional bank guaranty) በማስያዝ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
የጨረታ መክፈቻ
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ በተናጥል በፖስታ በማሸግ እንዲሁም በፖስታው ላይ ዋናውን “ዋና” ቅጂውን ደግሞ “ቅጂ” በማለት ለይተው በጉልህ በሚታይ ሁኔታ መጻፍ አለባቸው፡፡ ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ ላለማጭበርበር ቃል የሚገባበት ቅጽ ሞልተው ማሕተምና ፊርማ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ተጫራቾቹ ግለሰቦች ከሆኑ የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ኮፒ፣ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ካርድ ኮፒ (ካለ) እና ላለማጭበርበር ቃል የሚገባበት ቅጽ ሞልተው ማሕተምና ፊርማ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በአጠቃላይ በግልም ይሁን በድርጅት የሚቀርቡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻችሁን አሟልታችሁ በማቅረብ እና የጨረታ ማስከበሪያውን ለብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ እስከ 8፡00 (ስምንት ሰዓት) ድረስ ብቻ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ጨረታው በመስከረም 21/2019 ዓ.ም ከሠዓት በኋላ 8፡00 ሠዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዕድል አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
አገልግሎቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማስታወሻ፦ ተጫራቾች ከመጫረታቸው በፊት ተሽከርካሪዎቹን በግል መመልከትና ሁኔታቸውን ማረጋገጥ አስባቸው። አድራሻ፦ አዲስ አበባ ፒያሳ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ጎን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት
ስልክ፡ +251 0111266512 ኢሜይል፡ [email protected]
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-10-01
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-01 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
- Bid bond: የእያንዳንዱ ተሽከርካሪ መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
- Posted at: 2026-09-18T09:18:37.000Z
- Source: 2merkato