መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ያገለገሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ሠነድ ያላቸውና የሌላቸው 18 ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
★ Featured
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 126
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ያገለገሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ሠነድ ያላቸውና የሌላቸው 18 ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል!
ተሸከርካሪዎቹን ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 03 (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከፀበል መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን) ፊት ለፊት በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ተጫራቾች፣
- ለጨረታው የተዘጋጁትን ተሸከርካሪዎች በአዲስ ዘመን በወጣ ከ8ኛው ቀን ጀምሮ ከጧቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በአካል መመልከት ይቻላል።
- የጨረታውን ሰነድ ብር 500.00 (አምስ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣
- ሰነዱ የተጫራቾች መመሪያ በዝርዝር አካቶ የያዘ ስለሆነ ፎርሙ ከመሞላቱ አስቀድሞ በጥንቃቄ ሊነበብ ይገባል።
- የጨረታ ስነዱ በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ተሸከርካሪዎች ዝርዝር እና የጨረታ ማስገቢያ ፎርም የያዘ ሲሆን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ ለመግዛት የሚወስኑትን ተሽከርካሪ ይለያሉ፤ ስሙንና የሠሌዳኮድ ቁጥሩን ይይዛሉ።
- ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ (ማስያዣ) የሞሉትን ዋጋ 10% ሲፒኦ CPO ማሲያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ፎርም ላይ በመሙላት እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ ጋር አያይዘውና በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ጨረታው በይፋ ሊከፈት ግማሽ ሰዓት እስከሚቀረው ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 36 91 91 91 ወይም 09 75 26 41 59 መጠየቅ ይቻላል።
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-06-29
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-29 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጧቱ በ5፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Mekedonia Charity Association
- Buyer TIN: 0027054421
- Bid bond: 10% ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jun 14, 2026
- Posted at: 2026-06-15T07:42:08.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.