ዘመን ባንክ አ.ማ. በቁጥር 20 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ዘመን ባንክ አ.ማ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሽያጭ ማስታወቂያ

ዘመን ባንክ አ.ማ. በቁጥር 20 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የጨረታ ደንቦች፡-

1. ሞተር ሳይክሎቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ሞተር ሳይክሎቹን “ጎፋ መብራት ኃይል ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ት/ቤት” አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፤ ወይም በስልክ ቁጥር 0115-57-58-25/011 668 78 09 በመደወል ወይም ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት 12ኛ ፎቅ ላይ በንብረት እና ሎጂስቲክ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፣

2. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዋጋ መሙያ ቅጽ ከባንኩ የንብረት አሰተዳደርና ሎጂስቲክሰ መምሪያ በመግዛትና እና በመሙላት በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የመረጡትን ሞተር ሳይክል/ሎች ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 12ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

4. ጨረታው ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ በባንኩ ህንጻ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

5. ጨረታው በሚካሄድበት ዕለትና ሰዓት መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።

6. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ክፍያ መፈጸም አለበት። ይህን ባያደርግ ግን ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤

7. ባንኩ ንብረቱን በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው የመንግስት አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

8. ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያዎች፤ እንዲሁም ሞተሮቹን ከማስተካከል ከመጫንና ከማጓጓዝ ጋር የተያያዙ ማናቸውንምክፍያዎች ገዢው ይከፍላል።

9. ተጨማሪ የጨረታ ደንቦች የጨረታ ሰነድና የዋጋ መሙያው ቅጽ ላይ ተቀምጠዋል።

10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዘመን ባንክ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-07-01
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-07-02 09:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Zemen Bank S.C.
  • Buyer TIN: 0004608547
  • Buyer address: Josef Tito Street
  • Published: Jun 17, 2026
  • Posted at: 2026-06-17T07:45:17.000Z
  • Buyer website: https://www.zemenbank.com

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders