ፀደይ ባንክ አ.ማ. ንብረቶችን በግልፅ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ የኃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ደሳለዉ ወርቁ ረዴ ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዛቸዉንና ዝርዝር ሁኔታቸዉ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
የንብረቱ መገኛ፤ደረጃና ካርታ ቄጥር |
የጫረታዉ መነሻ ዋጋ |
|
1 |
ለአቶ ደሳለዉ ወርቁ ረዴ |
ለአቶ ደሳለዉ ወርቁ ረዴ |
ፍኖተ ሰላም ከተማ ቀበሌ 02 ካርታ ቁጥር 471-14-2014 መኖሪያ ቤት 200 ካ/ሜ |
6,712,996.89 |
|
2 |
ለአቶ ደሳለዉ ወርቁ ረዴ |
ለአቶ ደሳለዉ ወርቁ ረዴ |
አዉቶሞቢል ቻይና ቮልስዋገን ID6-CROZZ የሰሌዳ ቁጥር AA-02-C28536 chanssis ቁጥር LFVVB9E70N5160926 |
5,119,010.4 |
በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጫረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
2. የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል።
3. በጫረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ የድርጅት ከሆነ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት።
4. የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
5. በጫረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸመል።
6. የጫረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማንኛዉንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ወጭዎችን ገዢ ይከፍላል። ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር ዉል እንዲዋዋል ይደረጋል።
7. ተጫራቾች ቤቱን እና ተሸከርካሪዉን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
8. ጫረታዉ የሚካሄደዉ ሀምሌ 15/2018 ከጠዋቱ 3–5 የተጫራቾች ምዝገባ፤ ከ5 እስከ 6 ሰዓት ጫረታ በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታዉ ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል።
9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251 91 877 9825 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-07-22
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-07-22 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 21, 2026
- Posted at: 2026-06-22T11:07:05.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.