የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ፎርስ ተሸከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎቹን ከቀን 06/11/2018 ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-

1 የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤

2. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተሸከርካሪ ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማ ቅረብ የሚችል፤

3. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤

4. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤ 

5. ተሽከርካሪ አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሉ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤

6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤

7. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤

8. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤

9. ተጫራቹ ተሸከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፤

10. ተጫራቾች የሞሉትን የገልጽ ጨረታ ሰነድ ከቀን 06/11/2018 ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቀረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በቀን 09/11/2018 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

N.B:-

አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አሥራ አምስት ፐርሰንት) የሚከል መሆኑ ይታወቅ፤ መኪናውን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሸከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለመጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-16
  • Publishing entity: Ethiopian Revenue and Custom Commission Jigjiga Branch Bureau
  • Bid bond: 5%
  • Published: Jul 09, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders