ዘመን ባንክ አ.ማ. በቁጥር 10 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሽያጭ ማስታወቂያ
(በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ)
ዘመን ባንክ አ.ማ. በቁጥር 10 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ደንቦች፡-
1. ሞተር ሳይክሎቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሞተር ሳይክሎቹን “ጎፋ መብራት ኃይል ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ት/ቤት” አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፤ ወይም በስልክ ቁጥር 011 557-5825/ 011 668 7809 በመደወል ወይም ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት 12ኛ ፎቅ ላይ በንብረት እና ሎጂስቲክ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፣
2. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዋጋ መሙያ ቅጽ ከባንኩ የንብረት አሰተዳደርና ሎጂስቲክሰ መምሪያ በመግዛትና እና በመሙላት በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የመረጡትን ሞተር ሳይክል/ሎች ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፤00 ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 12ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
4. ጨረታው ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ በባንኩ ህንጻ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
5. ጨረታው በሚካሄድበት ዕለትና ሰዓት መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።
6. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ክፍያ መፈጸም አለበት። ይህን ባያደርግ ግን ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤
7. ባንኩ ንብረቱን በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው የመንግስት አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
8. ከስም ዝውውር፤ እንዲሁም ሞተሮቹን ከማስተካከል፤ ከመጫንና ከማጓጓዝ ከማጓጓዝ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ክፍያዎች ገዢው ይከፍላል።
9. ተጨማሪ የጨረታ ደንቦች የጨረታ ሰነድና የዋጋ መሙያው ቅጽ ላይ ተቀምጠዋል።
10.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ዘመን ባንክ አ.ማ
Sengatera, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212
Addis Ababa, Ethiopia
Tender details
- Deadline: 2026-07-27
- Publishing entity: Zemen Bank S.C.
- Published: Jul 14, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.