የፈረስ ቤት ኮንዶሚንየም ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር የጋራ መኖሪያ ህንፃውን የሕንፃ ጣሪያ፣ የጎሮንዳዮና የፍላሺንግ ጥገና ሥራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል
Description
የሕንፃ ጣሪያ የጎሮንዳዮና የፍላሺንግ ጥገና ሥራዎች
የጨረታ ቁጥር ፈ/ቤ/ኮ/03/2018
የፈረስ ቤት ኮንዶሚንየም ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር የጋራ መኖሪያ ህንፃውን የሕንፃ ጣሪያ፣ የጎሮንዳዮና የፍላሺንግ ጥገና ሥራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል።
ለጨረታው ውድድር የሚያስፈልገው መስፈርት፡-
1. በጨረታ መወዳደር የሚችሉት የሳኒተሪ እና የሕንጻ ሥራ ተቋራጮች
2. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፣ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ክሊራንስ፣ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሟልተው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ከማህበሩ ቢሮ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የቴክኒካል፣ የፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን በፖስታ አሽገዉ የተጫራቾች ፊርማ እና ማህተም አርፎባቸውና በአንድ ፖስታ አጠቃለው ማቅረብ አለባቸው።
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት ቆይቶ በ7ኛዉ ቀን በማህበሩ ቢሮ ይከፈታል።
6. ስለሥራው ሁኔታ በበለጠ ለመረዳት ሳይቱን ማየት ግዴታ ነው።
7. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ ከእንግሊዝ ኢምባሲ ወረድ ብሎ ወይም ከሲግናል ወደ እንግሊዝ ኢምባሲ በሚወስደዉ መንገድ
ስልክ፡ 09 13 51 78 03 / 09 40 39 15 60 / 011 658 1771
የፈረስ ቤት ኮንዶሚንየም ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-30
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት
- Bid opening: 2026-07-30 17:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት ቆይቶ በ7ኛዉ ቀን
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Feres Bet Condominium Owners Association
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 24, 2026
- Posted at: 2026-07-24T07:38:08.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.