Disposal Sale
ዘመድሁን አዳነ ሰርቲፋይድ ኦዲት ድርጅት የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ሂሳብ አጣሪ 61 ሰው የሚጭን ፊያት N3 ዘመኑ ያለፈበት ለረጅም ዓመታት የቆመ ለመለዋወጫ አገልግሎት የሚውል አውቶቡስ ባለበት ሁኔታ ማህበሩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ህዳር 02 ቀን 1957 ዓ.ም. የተቋቋመ ቢሆንም ማህበሩ ከ1966 ዓ.ም. ጀምሮ በንግድ ስራ ላይ አለመኖሩን ሰነዶች ያመለክታሉ፡፡ በአባላቱ ለፍርድ ቤት በቀረበ አቤቱታ ማህበሩን እንደገና ለማደራጀት ያልተቻለ በመሆኑ ሁኔታውን ለአባላቱ ቀርቦ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በተደረገ መደበኛ እና አስቸኳይ የአባላት ስብሰባ በአባላቱ አብላጫ ድምጽ ማህበሩ እንዲፈርስ ተወስኗል፡፡
በዚህም መሰረት የማህበሩ ሂሳብ የማጣራት ስራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
በሂሳብ ማጣራቱ ሂደትም ከማህበሩ አባላት በቀረበ ጥያቄ መሰረት የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር ንብረት የሆነ 61 ሰው የሚጭን ፊያት N3 ዘመኑ ያለፈበት ለረጅም ዓመታት የቆመ ለመለዋወጫ አገልግሎት የሚውል አውቶቡስ በባሌ ጎባ ከተማ በሐጂ መሀመድ አህመድ ሳላህ ግቢ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ይህን ንብረት ባለበት ሁኔታ ማህበሩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤ በመሆኑም ከላይ የተዘረዘረውን ንብረት ለመግዛት የሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 በባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር ስም በተከፈተው አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01322240761900 ገቢ በማድረግ አ.አ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ከማህበሩ ቢሮ ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
1) ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በራሱ ወጪ ባሌ ጎባ ከተማ በሐጂ መሀመድ አህመድ ሳላህ ግቢ በመገኘት መመልከት የሚችል፡፡
2) በጨረታው ለመሳተፍ ብር 50,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም በማህበሩ ስም የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር በተከፈተው አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01322240761900 ገቢ በማድረግ ማስያዝ የሚችል፡፡
3) በጨረታው አሸናፊ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ /ድርጅት በ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን በመክፈል ንብረቱን ሙሉ በሙሉ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ በራሱ ወጪ እና ኃላፊነት ማንሳት የሚችል፡፡
4) የጨረታ ሰነዱ መሰረት የሚገዛበትን ዋጋ እና የጨረታ ዋስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም ባንክ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ሰነድ በአንድ ላይ በማሸግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን አ.አ. ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመገኘት ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚችል፡፡
5) ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት የሚዘጋ ይሆናል፡፡ ጨረታው በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ.አ. ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 ይከፈታል፡፡
6) ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 313 167 / 0911 127 265 (አቶ ዘሪሁን ደጀኔ) ወይንም 0911 679 969 (አቶ ንጉሴ) በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ዘመድሁን አዳነ ሰርቲፋይድ ኦዲት ድርጅት
የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ሂሳብ አጣሪ
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-19 09:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ11 ቀን ቆይቶ በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
- Posted at: 2026-08-08T08:40:46.000Z