House, Building and Warehouse
የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ) ወይብላ ማርያም ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚገኘውን ዋልማ ታፍ ነዳጅ ማደያ በግልጽ ጨረታ አውጥቶ ለማወዳደር ይፈልጋል
Description
አገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ) በ2019 ዓ.ም. በጀት አመት ንብረትነቱ የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ) የሆነው ወይብላ ማርያም ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚገኘውን ዋልማ ታፍ ነዳጅ ማደያ ግልጽ ጨረታ አውጥቶ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡.
- በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል (የምትችል)፡፡
- በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሠ ንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው (ያላት)፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በስማቸው የተመዘገበ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቲ መኪና ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታውለመሣተፍ ከላይ በተራቁጥር1-5የተጠቀሱትንናየሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚገዙበት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ መግዛት ይችላሉ.
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመግዛት የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጋዜጣው በወጣበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በወጣው በ22ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 2 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሲል ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ልማት ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የዋግ ልማት ማኅበር (ዋስማ)
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-01 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Wag Development Association
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T08:41:27.000Z