Other Sales

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በመጀመሪያ ዙር የድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የመጀመሪያ ዙር የድርድር ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 መሠረት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ ከዚህ በታች ስሙ የተጠቀሰው ተበዳሪ ከባንኩ ለወሰደው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በመጀመሪያ ዙር የድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ

.

የተበዳሪው / የመያዣ ሰጪው ስም

ንብረቱ ሚገኝበት አድራሻ

የሚሸጠው ንብረት ዝርዝር መረጃ

የቀሪ ሊዝ

የድርድር መነሻ ዘመን ዋጋ (ብር)

የድርድር ደረጃ

ድርድሩ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት

1

ኤም ግብርና እና ኢንቨስትመንት /የተ/የግ/

በጋምቤላ /// መንግሥት፣ አኙዋክ ዞን፣ ጋምቤላ ከተማ

  • 500 ሄክታር የእርሻ መሬት (390 ሄክታር የለማ)
  • መኖሪያ፣ ቢሮ፣ የሠራተኛ መኖሪያ፣ ክሊኒክ እና መጋዘኖች፤
  • የእርሻ መሣሪያዎች (LANDINI ትራክተሮች ሞዴል DT100 እና DT125 የተመረተበት ዘመን 2014 እና 2015)
  • ተሽከርካሪዎች (Isuzu የጭነት መኪና እና TOYOTA ባለ ሁለት ጋቢና ፒካፕ)

38 ዓመት

33,047,344.67 (ሰላሳ ሦስት ሚሊዮን አርባ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ አርባ አራት ብር 67 ሳንቲም)

1 ዙር ድርድር

ጋምቤላ ዲስትሪክት /ቤት፣ ነሐሴ 28 ቀን 2018 . ከቀኑ 800 እስከ 1000 ሰዓት

2. የድርድር መመሪያዎች

1. ተጫራቾች ንብረቱን ከድርድሩ ቀን በፊት መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፣ ለጉብኝት ከባንኩ ጋምቤላ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ፕሮግራም መያዝ ይኖርባቸዋል።

2. በድርድሩ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የድርድሩን መነሻ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በማስያዝ መቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ድርድሩ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ንብረቱን በጥሬ ገንዘብ የሚገዛ ከሆነ፣ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ካልከፈለ የድርድሩ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።

4. ንብረቶቹ ከቀረጥ ነፃ የገቡ በመሆናቸው፣ አሸናፊው ተጫራች ተመሳሳይ የቀረጥ ነፃ መብት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። የቀረጥ ነፃ መብት የሌለው ገዢ ከሆነ ግን፣ የመንግሥትን የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ አለበት።

5. በድርድሩ አሸናፊ የሆነ ተጫራች በሕግ የተወሰነውን 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ተያያዥ ክፍያዎችን ይከፍላል።

6. ተጫራቾች በድርድሩ ለመሳተፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የነዋሪነት መታወቂያ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ድርድሩ ባልተሳካላቸው ተጫራቾች ያስያዙት የሲፒኦ (CPO) ዋስትና ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

8. ድርድሩ በሠንጠረዡ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይካሄዳል።

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ድርድሩን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 475 512 577 / +251 475 512 588 / +251 471 518 284 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-03 14:00
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 10%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T11:03:34.000Z
← Back to all tenders