Steel Raw Materials and Products

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ 200 ቶን ቁርጥራጭ ብረታብረት አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ አግጨ /001/ኦኩስፋ-2/2018 ዓ.ም

1.በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ 200 ቶን ቁርጥራጭ ብረታብረት አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ60 ቀን የባንክ ዋስትና BID BOND/ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

3. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 አስራ አምስት) ቀን አየር ላይ ውሎ በአስራስድስተኛ ቀን ይከፈታል፡፡ የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00- 6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተመለከተው ነው፡-

1.1 አሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነአ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ አንደኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 1371/103 ውስጥ፡፡ ስልክ ቁጥር፡ 09-91-14-94-85 ወይም 09-86-86-27-66 አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ

6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለዕያንዳንዱ ሎት የማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

7. የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪ ቢሮ ነው፡፡

8. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው፡፡

9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው፡፡

10. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ…..አዲስ አበባ ገዥ ማስተባበሪያ ቢሮ

Tel-0940209464......Tel: 09-91-14-94-85 ወይም 09-86-86-27-66

ሀይል ውሃ............ አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ……አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 አስራ አምስት) ቀን
  • Bid opening: 2026-08-26 17:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 አስራ አምስት) ቀን አየር ላይ ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Omo Kuraz No-2 Sugar Factory
  • Bid bond: 100,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T12:35:44.000Z
← Back to all tenders