Textile, Garments and Uniforms
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ጉምሩክ ኮሚሽን የተለያዩ እቃዎችን በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 13/12/2018 እና 16/12/18 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም ለአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባለበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ስልክ ቁጥር 022 224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 13/12/2018 እና 16/12/2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ መክፈቻ ቦታ: በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለቡት ወይም በታዛቢዎች ይከፈታል።
- በጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርበታል።
- ከላይ በተ.ቁ7 በተገለጹት ቀናት ወስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች በጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የጨረታ ቦታ |
የጨረታው ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና |
|
1 |
ቃሊቲ/ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ |
በጉምሩክ ኮሚሽን ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ፣ መነፅር፣ ጌጣጌጥ፣ የሳሙናፋብሪካ አካል ማሽነሪ፣ መሰላል ብረቶች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች |
ለግልጽና የሐራጅ ጨረታ 13/12/2018 እና 16/12/2018 እስከ ጠዋቱ 3፡45 |
ለግልጽ ጨረታ 13/12/2018 እና 16/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 13/12/2018 እና 16/12/2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል |
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-22
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-08-22 11:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Afar
- Publishing entity: Ethiopian Revenue & Customs Authority Awash Branch
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-12T11:12:41.000Z