Building and Finishing Materials

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ፌሮ ብረቶች፣ ሴራሚኮች፣ ጎማዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የውሃ ዕቃዎች የሻወርና የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች እና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ዕቃዎችን ለመሸጥ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ጋምቤላ/ስተአ/003/2018

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ፌሮ ብረቶች፣ ሴራሚኮች፣ ጎማዎች፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የውሃ ዕቃዎች የሻወርና የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች እና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች፡-

1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሸያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጋምቤላ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ከፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከነሐሴ 05/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።

2, በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugee and Returnee Service/ በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና [Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ማንኛውም ተጫራጭ ከነሐሴ 05/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም።

4. ጨረታው ጋምቤላ በሚገኘው የአግልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ነሐሴ 14/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

5. የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

6. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ1ዐ ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።

7, በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአግልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር +251 91 127 8481 ወይም +251 91 046 4495 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-20
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-20 10:30
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Refugee and Returnee Service
  • Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T07:45:20.000Z
← Back to all tenders