Textile, Garments and Uniforms

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት የቢሮውን የሥራ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥዎችን በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ፍ/ቢ/ጨ/ቁጥር 001/2019

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት የቢሮውን የሥራ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥዎችን በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መፈጸም ይፈልጋል።

ተቁ

የእቃዎች ግዥ

ተቁ

የአገልግሎት ግዥ

1

ሎት አንድ (Lot 1)

የአቃቤያነ ህግ ለወንድ እና ሴት የፕሮቶኮል ሙሉ ልብስ ሸሚዝ፣ ጫማና የችሎት ካባ ግዥ እና የሥራ ልብስ ለጥበቃ፣ ለጽዳትና ተላላኪ እንደ 3/4 ጋዎን፣ ሽርጦች፣ ቆዳ ጫማዎች ወዘተ ዝርዝሩን ሰነዱን ይመልከቱ

1

 

ሎት አስር (lot 10)

የኮምፒውተር ፕሪንተርና ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በመፈተሸ የጥገና አግልግሎት ግዥ ለአንድ አመት ውል ገብቶ ከነ መለዋወጫ እቃዎች በማቅረብ የሚጠግን

2

ሎት ሁለት (lot 2)

አላቂ የቢሮ ዕቃዎች (የጽህፈት መሣሪያዎች) ግዥ እንደ ቀለሞች፣ ወረቀቶች፣ማስታወሻ ደብተር ወዘተ

2

 

 

 

ሎት አስራ አንድ (Lof 11)

የጄኔሬተር፣ የሊፍት እና የውሃ መሳቢያ ጀኔሬተር ጥገናና ሰርቪስ ግዥ ዝርዝሩ በሰነዱ ውስጥ ተካቷል።

3

ሎት ሶስት (lot 3)

 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ (ልብስ ማጠቢያ፣ የምግብ ማሞቂያ፣ ፍሪጆች፣ ቴሌቪዥኖች ወዘተ)

 

3

 

 

 

ሎት አስራ ሁለት (Lot 12)

የመስሪያ ቤቱን የሠራተኞች ካፍቴሪያ ለ1 አመት ውል ገብቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የተረበ የአገልግሎት ግዥ

4

ሎት አራት (lot 4)

የጽዳት እቃዎች ግዥ(ላርጎ፣ በረኪና፣ ዲቶል፣ መወልወያ፣ ቪም፣ ወዘተ)

4

 

 

ሎት አስራ ሶስት (Lot 13)

የስራ ልብስ ስፌት የአገልግሎት ግዥ

5

ሎት አምስት (lot 5)

የእንጨት ውጤቶች ግዥ

(የህጻናት ማቆያ አልጋ፣ የአስተያየት/ ጥቆማ መስጫ ሳጥኖች፣ የካፍቴሪያ የመመገቢያ ጠረንጴዛ፣ የካፍቴሪያ ወንበር፣ የጫማ ማስቀመጫ ሼልፍ (ለዴኬየር) የህጻናት ልብስ ማስቀመጫ ሼልፍ ወዘተ)

5

 

 

 

 

ሎት አስራ አራት (Lot 14)

ሁለገብ የጥገና አገልልግሎት ግዥ(የበር፣ የመስኮት፣ የመጋረጃ፣ የሼልፎች፣ የጠረንጴዛና ወንበር ጥገና)ወዘተ

6

ሎት ስድስት (Lot 6)

ለስብሰባዎች የታሸገ ውሃ በሩብና በግማሽ ሊትር መጠን ለአንድ አመት ውል ገብቶ የሚያቀርብ ግዥ

6

 

ሎት አስራ ስድስት (Lot 16)

በዴኬየር ክፍል ውስጥ የሚከናወኑ የዕቃ አቅርቦትና የፓርቲሽን እና የጥገና ስራዎች(የቀለም መቀባት፣ኪችን ካቢኒት ስራ፣ የፓርሽን ስራ ወዘተ)

7

ሎት ሰባት (lot  7)

የኤሌክትሪክ፣ የቧንቧና የአትከልት ዕቃዎች ግዥ ዝርዝሩ በሰነዱ ላይ ተካቷል።

 

 

 

 

 

 

8

ሎት ስምንት (lot 8)

ሕትመትና የሕትመት ውጤቶች ግዥ(ባነር፣ ዲጂታል ማስታወቂያ፣ የሰራተኞች መታወቂያ፣ ምስክር ወረቀት ወዘተ)

9

ሎት ዘጠኝ (lot 9)

የመኪና ጌጣጌጦች፣ ልብሶች፣ ቸርኬዎችና ባትሪዎች ግዥ የመኪና ወንበር ልብስ፣ ከሪክና ጎማ መፍቻ፣ የዳሽ ቦርድ ቅባት ወዘተ

10

ሎት አስራ አምስት (lot 15)

የቢሮ መስተንግዶ እቃዎችና የዴኬየር ዕቃዎች ግዥ ዝርዝሩን በሰነዱ ውስጥ ተካቷል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ።

4. ከመንግሥት ግዥ የታገዱ ያልሆኑ እና ውል ለመፈጸም የሚያስችል ሙሉ የሕግ ችሎታ ያላቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ፣ 7ኛ ፎቅ፣ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመገኘት መግዛት ይችላሉ።

6. ናሙና እንዲቀርብባቸው የተጠየቁ ዕቃዎችን ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. አሸናፊው ድርጅት የውል ስምምነት ከመፈረሙ በፊት የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።

9. ተጫራቾች የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነዶቻቸውን (ኦርጅናል እና ኮፒ) ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ሰነዱ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።

10. ቢሮው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የግዥ መጠኑን እስከ 25% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን በጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ፣ በዚያው ዕለት 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። (ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል)።

12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ማስታወቂያ ከወጣው በተጨማሪ ብዙ ዝርዝር እቃዎች የያዘ በመሆኑ ሰነዱን በአጽንኦት በመመለከት ለእያንዳንዱ እቃ ዋጋ መሙላትዎን ያረጋግጡ።

 ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ ቁጥር፡ 011-515 9548

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-27 09:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Justice Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T08:34:03.000Z
← Back to all tenders