Other Sales

የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎውሺፕ ኢንተርናሽናል (CMFI) ሲጠቀምባቸው የነበሩትን ሕንፃዎች፤ ቪላ ቤቶች፣ አፓርትመቶች እና ተያያዥ ንብረቶችን በጥቅል ባሉበት ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት (CSO) ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ (ለመሸጥ) ይፈልጋል

Description

የንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎውሺፕ ኢንተርናሽናል (CMFI) ሲጠቀምባቸው የነበሩትን ሕንፃዎች፤ ቪላ ቤቶች፣ አፓርትመቶች እና ተያያዥ ንብረቶችን በጥቅል ባሉበት ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት (CSO) ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ (ለመሸጥ ) ይፈልጋል::

1.1 ንብረቶቹ የሚገኙበት ስድራሻ፡- በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ኖኖ ወረዳ የቤት ቁጥር አዲስ ወይም በተለምዶ አጠራር ታጠቅ ደስታ መንደር ወደ ፌስቱላ ሆስፒታል ሕሙማን ማገገሚያ ማዕከል በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ይገኛል::

1.2 ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለግ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት መወዳደር ይችላል::

1.3 ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመንና ሪፖርተር ጋዜጦች ላይ ከወጣበት ከነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአስራ አምስት የሥራ ቀናት በስራ ስዓት ኦርጅናል ማህተም እና ፊርማ ያለበትን የጨረታ ስነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር 280 በተለምዶ ዘነበ ወርቅ አካባቢ ታቦት ማደሪያ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮው በአካል መጥተው መግዛት ይቻላል::

1.4 የጨረታው ሰነዱ (የጨረታ ቁጥር 04/2018) ብዙ ዝርዝር ጉዳዮችን _ የያዘ መሠረታዊ ሰነድ በመሆኑ መግዛት እጅግ አስፈላጊ ነው::

1.5 ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ከጨረታው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ በመንተራስ 20%(ሀያ በመቶ) የማያንስ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ኤም. ኤፍ.አይ (CMF) ስም በባንኩ በተረጋገጠ ክፍያ መዘዣ (CPO) በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: CPO (ሲ.ፒ.ኦ) ከ 20%(ሀያ በመቶ) ካነሰ  የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል::

1.6 የጨረታው ሳጥን የሚቀመጠው በተ.ቁ 1.1 ተቀምጦ ባለው አድራሻ ንብረቶቹ በሚገኙበት ታጠቅ ደስታ መንደር የቤት ቁጥር አዲስ ኖኖ ወረዳ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ሸገር ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ነው::

1.7 የጨረታው ሳጥን ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የእለቱ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዉ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል::

1.8 አሸናፊው ወዳያውኑ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን በ15 ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን መረከብ አለባቸው፡

1.9 በተራ ቁጥር 1.7 መሰረት ጨረታውን አሸንፈው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከፍለው የማይረከቡ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ቢድ ቦንድ _ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡ የጨረታው አሸናፊ ከስም ዝውውር ጋር የተያያዘው ግብር እና ማንኛውም በመንግስት የሚጠየቁትን ክፍያዎች ይሸፍናሉ:: ውዝፍ ዕዳ ካለ ግን አጫራች(ሻጭ) ይከፍላል::

1.10 የጨረታው ለማያሸንፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ(CPO) የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::

1.11 የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ማስታወቂያው በጋዜጦች ከወጣበት ከነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) እስከ ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የሚቆይ ይሆናል::

1.12 በተጨማሪም በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱት የተጫራቾች መመሪያን ትኩረት ሰጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ከተጫራቾች ይጠበቃል::

1.13 የክርስቲያን ሚሽነሪ ፌሎሽን ኢንተርናሽናል (CMF) የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ ፖ ሳ.ቁ 2920 አዲስ አበባ
ስ.ቁ. 0911 20 64 04 ወይም 0944 35 45 19


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-08 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Christian Missionary Fellowship International (CMFI)
  • Bid bond: 20%(ሀያ በመቶ) የማያንስ
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T11:50:49.000Z
← Back to all tenders