Food Items and Drinks
ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ለተለያዩ ዝግጅቶች እና መደበኛ የቢሮ አገልግሎቶች የሚሆን 1/2 (ግማሽ) ሊትር የታሸገ ውሃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በውል መሠረት መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ለተለያዩ ዝግጅቶች እና መደበኛ የቢሮ አገልግሎቶች የሚሆን 1/2 (ግማሽ) ሊትር የታሸገ ውሃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በውል መሠረት መግዛት ይፈልጋል።
የተወዳዳሪዎች መስፈርቶች
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ማሟላት አለባቸው፡
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
- የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
- የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአቅራቢዎች ዝርዝር (Supplier List) የተመዘገቡ።
የጨረታ ሰነድ አገዛዝ
ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመስቀል አደባባይ በሚገኘው ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
የጨረታ ማስከበሪያ
ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በCPO ወይም ቅድመ ሁኔታ ባልተቀመጠበት የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ስም አዘጋጅተው ከቴክኒክ ስነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታ ጊዜ እና መከፈቻ ሁኔታ
- አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ፡ ከነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይቆያል።
- ጨረታው የሚዘጋበት ጊዜ፡ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8:30 ሰዓት።
- ጨረታው የሚከፈትበት ጊዜ፡ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8:35 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:-
- ቦታ፡ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ፣ ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት
- ስልክ፡ +251 11 515 1693
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-08-31 14:35
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Exhibition Center & Market Development Enterprise
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Reporter (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T12:10:59.000Z