Vehicle and Machinery Foreclosure
ብርሃን ባንክ አ.ማ. ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የመተካት ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል በዚሁ መሰረት ያገለገሉ ስድስት አውቶሞቢል እና ሶስት ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ/ሎ_02/19
ብርሃን ባንክ አ.ማ ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የመተካት ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል በዚሁ መሰረት ያገለገሉ ስድስት አውቶሞቢል እና ሶስት ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ ቤት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
|
ተ.ቁ |
በጨረታ የቀረበ ያገለገሉ ተሽከረካሪዎች |
የተመረተበት ዓ/ም (አውሮፓውያን አቆጣጠር) |
ብዛት |
|
1 |
አውቶሞቢል ሃውንዳይ ‘Grand’ i10 |
2014 እና 2016 ዓም |
6 |
|
2 |
ሞተር ሳይክል ሱዚኪ TS ‘185’ |
|
3 |
1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሜክስኮ ዲ_አፍሪክ ሆቴል ጀርባ በሚገኘዉ የብርሃን ባንክ ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
2 ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈዕሠዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ የባንክ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ሕንፃ 2ተኛ ፎቅ ከፕሮፐርቲ ከሚገኘዉ ከባንኩ ሰንጋተራ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ፣ እንዲሁም ሰንጋተራ ቅርንጫፍ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ ከነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ከአንድ በላይ ተሸከርካሪ መግዛት ከፈለጉ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር በተገለጸዉ መሰረት ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 10% ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ C.P.0. ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ተሽከርካሪዎች አንድ እና ከዛ በላይ በተናጠል ተወዳድረዉ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ክጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ በተናጠል በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ CPO ጋር አያይዘዉ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት፣ የጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
6 ጨረታዉ ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኘበት የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጀስቲክስ ቢሮ ይከፈታል።
7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ያሸነፉባቸዉን ተሸከርካሪ/ተሽከርካሪዎች ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለዉ በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለጸላቸዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
9. የጨረታው አሸናፊ ላሸነፈበት ተሽከርካሪ/ተሽከርካሪዎች ከስም ማዛወሪያ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል።
10. ጨረታዉ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለዉ።
11. ለአዉቶሞቢሎቹ ግዥ በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ አሽናፊዎች ብድር ሊመቻች ይችላል።
12. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 663 1729 /09 98 45 44 24/ 09 98 41 15 23 ደዉለዉ ማግኘት ይችላሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-07 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Berhan Bank S.C.
- Bid bond: 10% ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Reporter (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T13:06:15.000Z