Transportation Service

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከቆቃ አዳማ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የሚችል በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/03/2019

1. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከቆቃ አዳማ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የሚችል በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና  የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ካሸሪ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 14 መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የትራንስፖርት አገልግሎት በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/ NCB/03/2019 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 70,000.00 (ሰባ ሺህ ብር ብቻ) ለ60 (ስልሳ) ቀናት የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው።

6. ጨረታው ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ይከፈታል።

7. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 57 40 11 መደወል ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-27 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Power
  • Bid bond: 70,000.00 (ሰባ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T07:30:40.000Z
← Back to all tenders