Disposal Sale

ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናዜሽን የድርጅቱን በዋናው መ/ቤት ውስጥ የሚገኝ ያገለገለ የመስክ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገለ መኪና ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናዜሽን የድርጅቱን በዋናው መ/ቤት ውስጥ የሚገኝ ያገለገለ የመስክ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 ስለሆነም፡-

ተጫራቾች፡

  1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መኪናውን የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት በሚገኙበት አድራሻ ጉርድ ሾላ ኤኤች ኤፍ ህንፃ ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን መኪና ወይም ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አስርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የመኪናውን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /column/ ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአኀዝና በፊደል ያለ ሰርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ አዲስ አበባ ከተማ ጉርድ ሾላ ኤኤች ኤፍ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት አስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራጩ ወይም በተወካዩ መፈረም አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው በተለያዩ የማስታወቂያ ሰሌዳዎችና በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07(ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ03 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ5ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) እየከፈሉ ባሉት 07 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ሰባተኛው ቀን 6፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በተለያዩ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ዐ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በሰባተኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 10፡00 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፊት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነድ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ድርጅቱ ስለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011- 647 83 82/0920523734/0911236537 ወይም በአካል

በመምጣት መጠየቅ ይቻላል፡፡ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ጉርድ ሾላ ኤ.ኤች. ኤፍ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 304

ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናዜሽን

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-24
  • Bid closing time: 15:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 (ሰባት) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በሰባተኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-24 16:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 (ሰባት) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በሰባተኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Rift Valley Children and Women Development Organization
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T11:00:18.000Z
← Back to all tenders