Other Sales

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር በሚገኘው ቢሮ የመለዋወጫ ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለ2ተኛ ጊዜ የወጣ የመለዋወጫ ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ግ/ጨ/ቁጥር 49/2018

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር በሚገኘው ቢሯችን የመለዋወጫ ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች የሚሸጡትን መለዋወጫዎች ዋናው መ/ቤት በሚገኘው ስቶር በአካል በመገኘት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት በመመልከት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይቻላል።
  2. በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆነ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን  በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ። ነገር ግን በማህበር ለመወዳደር የሚፈልግ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ በፍትህ ተቋም የተሰጠውን ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት  ለፊት በሚኘው ቢሯችን ቢሮ ቁጥር 02 በሚገኘው ቢሯችን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ሠዓት ማስገባት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /bid bond/ የተጨማሪ እሴት ታክስን 15% ጨምሮ የሚገዙበትን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በባንክ ማስያዥያ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ቼክ እንደ ማስያዥያ ማቅረብ ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  6. የተሰጠው ዋጋ በሎት ተደምሮ የሚገኘው ድምር ውጤት ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል።
  7. ሆኖም የድምር ዋጋው ከፍተኛ ቢሆንም ድርጅቱ ከተመነው የመሸጫ ዋጋ ያነሰ ሆኖ ከተገኘ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኖ ሊመረጥ አይችልም።
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙትን የጨረታ ማስያዣ ለኮርፖሬሸኑ ገቢ ይሆናል።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በከፈሉ ማግስት ጀምሮ እቃውን በ15 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው። ሆኖም ግን በተባለው ቀን የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት ሲፒኦ ተወርሶ ኮርፖሬሽኑ የሚያዋጣው ከሆነ 2ኛ ለወጣው ተጫራች የሚሸጠው ይሆናል።
  10. ጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለውሃ ስራዎች ኮርፓሬሽን የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000265163223 አስገብተው ማስረጃ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  11. ከገዥው በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ እቃውን መረከብ ባይችል ያጋጠመውን ችግር ከበቂ ማስረጃ ጋር በጽሑፍ አመልክቶ የድርጅቱ የሚመለከተው ኃላፊ ሲፈቅድ ብቻ የርክክብ ጊዜው ሊራዘም ይችላል።
  12. የሚሸጡት መለዋወጫዎችን በተመለከተ የሚኖር ማንኛውንም ወጭ በአሸናፊው የሚሸፈን በመሆኑ በዚህ አግባብ ግዴታ የሚገባ ይሆናል።
  13. በሎት የተቀመጡት ማጠቃለያ የዕቃዎች ድምር ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል።
  14. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ - በስልክ ቁጥራችን 09-30-35-24-01 እና 09-85-07-75-18 እንዲሁም በኮርፖሬሽናችን ዌብሳይት

www.wwc.com.et  እና https://www.facebook.com  እንዲሁም

ቴሌግራም https://t.me/WaterWorksCorporationofficial  መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የውሃ ሥራዎች  ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Water Works Construction Enterprise
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T12:48:25.000Z
← Back to all tenders