Equipment and Accessories

ቲ.ኤስ.ዲ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የስልክ ቀፎዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018

ቲ.ኤስ.ዲ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከሲመንስ (SIMENS) ድርጅት በተለያየ ጊዜያት ያስመጣቸውን እና የገዛቸውን የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የስልክ ቀፎዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል ከዚህ በታች በተመለከተው የጨረታ መመሪያ መሰረት በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

1. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተመለከተው የድርጅቱ ፋይናንስ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዐት የጨረታውን ሰነድ በብር 500 (አምስት መቶ) ሳሪስ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

2. ማንኛውም ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዕቃዎቹ በሚገኙበት ሳሪስ ካዲስኮ ህንፃ ጌም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመሄድ ዘወትር በስራ ሰዐት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዐት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ሊገዙት የሚፈልጉትን እቃ LOT የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታው ዶክመንት ውስጥ በተዘጋጀው የመሸጫ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት ለእያንዳንዱ LOT በተለያየ እና በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ሳሪስ ካዲስኮ ህንፃ ጌም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። 

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።

5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት LOT ዕቃ የጨረታ ማስረከቢያ የሚጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ በመቶ(2%) በቲ.ኤስ.ዲ ስም በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ነሃሴ 23 ቀን 2018ዓ.ም 4፡00 ይዘጋል። የጨረታው አሸናፊዎች ዝርዝር ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ በድርጅቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይለጠፋል። አሸናፊውም ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብና ማንሳት ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስረከቢያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ሳሪስ ካዲስኮ ህንፃ ጌም ሆቴል አከባቢ
ስልክ፡ +251 11 440 33 55/56 ሞባይል፡ +251 910 27 44 20
ኢሜይል፡ [email protected] 
ዌብሳይት፡ www.tsdethiopia.com 
ቲ.ኤስ.ዲ ሺንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-29 10:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: TSD Engineering Plc
  • Buyer TIN: 0000015920
  • Buyer address: ሳሪስ ካዲስኮ ጌም ሆቴል አካባቢ
  • Bid bond: 2% ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T15:07:46.000Z
  • Buyer website: https://www.tsdethiopia.com
← Back to all tenders