Disposal Sale
አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2020 ሞዴል ያገለገለ ጣልያን አይቪኮ ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የተሽከርካሪ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/ የም/አም/ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ሽያጭ /0005/2026
አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2020 ሞዴል ያገለገለ ጣልያን አይቪኮ (Model 50C15/E3 Year: 2020፣ Chassis no.: EBPBCAHAALD000016፣ Motor no.: FICE3481J3827326፤ Clour: White፣ Vehicle type: Bus፣ CC: 2998 ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት በጨረታዉ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያመሟሉ ማንኛዉም ተጫራቾች ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መጫረት ይችላሉ፡፡
1. ማንኛዉም የመጫረት ፍላጎት ያለዉ በጨረታዉ ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን ሲያቀርቡ ለተጫረቱበት ተሸከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 % (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሲፒኦ ዉጪ የሚያቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለዉም፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ተሽከርካሪው አዳማ በሚገኘዉ የድርጅቱ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊዉ ተለይቶ ከታወቀ በኃላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
5. የጨረታዉ አሸናፊ ለተሽከርካሪዉ የሚከፈሉ ማንኛዉንም የመንግስት ክፍያዎችን ሁሉ ይሸፍናል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራትች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
7. የጨረታዉ አሸናፊ መሆኑ የተገለፀለት ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 10% (አስር በመቶ) እንደውል ማስከበሪያ ይቆጠራል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የገባውን ውል ካልፈፀመ ለጫረታ መስከበሪያ የተየዘው ዋስትና እንደ ውል ማስከበሪያ ተቆጥሮ የተያዘዉን ገንዘብ አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ መምርያ አዳማ ወይንም አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
9. ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ 16ኛዉ የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን አዳማ ከተማ በሚገኘዉ የድርጅቱ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰዉ ቀን እና ሰዓት ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተሞላ ወይንም በሌላ ወረቀት ላይ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለዉም፡፡
11. የጨረታዉ አሸናፊ የሚለየዉ ባቀረበዉ የመግዣ ዋጋ መሠረት ብቻ ነዉ፡፡
12. የጨረታዉ አሸናፊ ጨረታዉን ማሸነፉ በተገለጸ በ7 ቀናት ዉስጥ በአካል ቀርቦ ዉል መፈፀም አለበት፡፡
13. የጨረታዉ አሸናፊ ዉል እንዲፈፅም በተገለፀለት በ 7 ቀናት ዉስጥ ቀርቦ ዉል ባይፈፅም ድርጅቱ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘዉን ዋስትና ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል፡፡
14. ድርጅቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፤- 011-639-2511/093-029-3626
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ 16ኛዉ የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-02 14:30
- Bid opening (note): ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ 16ኛዉ የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Alvima Foods Complex PLC
- Buyer TIN: 0023572660
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Reporter (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T12:52:14.000Z