Other Sales

የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

Description

የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ስማቸው ከዚህ በታች የተመለከቱት ድርጅቶች በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1268/2014 አንቀጽ 12 መሰረት ከሠራኛው መደበኛ የወር ደመወዝ ላይ ተገቢውን የጡረታ መዋጮ ቀንሰው እና የድርጅቱን ድርሻ መዋጮ ጨምረው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ገቢ ባለማድረጋቸው አስተዳደሩ በአዋጅ ቁጥር 1268/2014 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 3 በተሠጠው ስልጣን እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው መመሪያ ቁጥር 1086/2017 መሠረት የድርጅቶቹን ሃብት በግልጽ ጨረታ በመሸጥ ውዝፍ ጡረታ መዋጮ ዕዳው እንዲሰበሰብ ወስኗል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

ተራ ቁጥር

 

ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ዕዳው የሚፈለግበት ድርጅት ሥም

 

በቀጣይ የሚታሰብ ወለድ እና ቅጣት ሳይጨምር ከድርጅቱ የሚፈለገው የጡረታ መዋጮ ዕዳ መጠን በብር

የማሽነሪው አይነት

 

የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር

የድርጅቱ ሃብት የሚገኝበት አድራሻ

 

የጨረታ መነሻ ዋጋ

 

1

 

ቤዛዓለም ኔትዌር የተ የግ/ማ

 

3,621,898.70

 

 

------

አቃቂ ቃሊቲ /ከወረዳ 7 ልዩ ስሙ እንዱስትሪ ሰፈር

24,519,220,27

 

1 ስለሀብቱ አሻሻጥ ከአስተዳደሩ የግዥ ዳይሬክቶሬት ወይም ከህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ከግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በግልጽ በማስፈር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው አድራሻው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ ቤት በማለት አስፍረው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሠዓት እንዲሁም ከሠአት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/10 ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡

5. ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በ4፡15 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስተዳደሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የእረፍት ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

6. ተጫራቾች ይዞታውን በግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ ቤት በሚያመቻቸው ፕሮግራም በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡

7. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዥው ዋጋ ጋር ታስቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባለት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈል ሃብቱን መረከብ አለበት፡፡

8.የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ5 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለአስተዳደሩ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱ ይሠረዛል፡፡

9. ከሽያጩ ጋር በተያያዘ የሚከፈሉ ግብርና ታክሶች፣ የስም ማዛወሪያ እንዲሁም ሌሎች ማናቸውም ህጋዊ ወጪዎች በገዢ ይሸፈናሉ፡፡

10. አስተዳደሩ ስለሀብቱ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-09-08 12:00
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡15 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Private Companies Employees Social Security Agency
  • Buyer address: መገናኛ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ወይም ከሙሉጌታ ዘለቀ ህንጻ አጠገብ
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T09:47:47.000Z
← Back to all tenders